የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከሰላም ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር በተቋሙ ተግባርና ተልዕኮ እና ቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ተግባራት ላይ ውይይት አካሂደዋል።
የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከሰላም ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር በተቋሙ ተግባርና ተልዕኮ እና ቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ተግባራት ላይ ውይይት አካሂደዋል።
ታህሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከሰላም ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር በተቋሙ ተግባርና ተልዕኮ እና ቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ተግባራት ላይ ውይይት አካሂደዋል።
ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የዛሬው ውይይት ተቋማችን እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት ለማጠናከር እና የተሰጠንን ሀገራዊ ኃላፊነት በላቀ ሁኔታ ለመወጣት ያለመ ነው ብለዋል።
በቀጣይ ሰው ተኮር የሆነ አሰራር እንከተላለል ያሉት ክቡር አቶ መሀመድ በቴክኖሎጅ የተደገፉ ስርዓቶችን በመዘርጋት ተቋሙን ውጤታማ የሚያደርጉ ተግባራት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ገልፀዋል።
ሀገራችን የምንሰጣትን ነው የምትሰጠን ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ያለንን ዕውቀት፣ ጊዜና ሀብት ያለ ስስት ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት ልናበረክት እንደሚገባም አሳስበዋል።
ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ አክለውም ተቋማዊ አሰራር ግልፅ እና ተጠያቂነት ሊኖራቸው ይገባል ያሉ ሲሆን ህሊናን፣ መረጃን እና ህግን መሰረት ያደረጉ አሰራሮችን ተግባራዊ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል ።
በውይይቱ ላይ ሊስተካከሉ እና በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ሰራተኞች ሃሳባቸውን አንስተዋል።