የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሰላም ሲቨል ማህበራት ኅብረት አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ
የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሰላም ሲቨል ማህበራት ኅብረት አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ
ታህሣሥ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሰላም ሲቨል ማህበራት ኅብረት አመራሮች ጋር በሰላም ግንባታ እና በብሔራዊ መግባባት ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል።
የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በውይይቱ እንደተናገሩት በሰላም ግንባታ ላይ የሲቨል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው እንደ መንግስት መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በራሳቸው ቁመው ለሰላም እና ለሀገር ግንባታ እንዲሰሩ የመንግስት ፍላጎት ነው ብለዋል።
የሰላም ሚኒስቴር ሥራዎች ዘርፈ ብዙ ናቸው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴዔታው የሰላም ባለቤት ሁሉም እንደመሆኑ መጠን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል በቀጣይም ይህን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በቅንጅትና በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ያሉት ክቡር ዶ/ር ከይረዲን በሀገራችን ብዙ የሲቨል ማህበራት ድርጅቶች አሉ እነዚህ ድርጅቶች በሰላም ላይ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
ከኢትዮጵያ የሰላም ሲቨል ማህበራት ኅብረት የተገኙት አመራሮች በበኩላቸው "ሰላም ላይ መስራት ራስ ላይ መስራት እንደመሆኑ ስለ ሰላም ለመስራት እድል ማግኘታችን ለእኛ ትልቅ ትርጉም አለው" ብለዋል።