ብሔራዊ መግባባትና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ስልጣን እና ተግባር መካከል በዋናነት በሀገሪቱ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ማስፈን፣ ብሔራዊ መግባባትና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን ማጎልበት፤ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ሀገራዊ አንድነትና መግባባትን የሚያጎለብት እና በኅብረተሰቡ መካከል የሰላም፣የመከባበርና አብሮ የመኖር ባህል እንዲዳብር የግንዛቤ ስራዎችን ማከናወን ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡

ብሔራዊ መግባባትና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት መፍጠርና ማጎልበት አንዱ የሰላም ሚኒስቴር ዋና ተልዕኮ ሲሆን በሀገራችን ውስጥ ለግጭትና አለመግባባቶች መንስኤ ይሆናሉ ተብለዉ የሚታሰቡ መሰረታዊ/ወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግባባትና መተማመን እንዲፈጠር ማድረግ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ማለትም፤ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች፤ ብሔራዊ ጥቅም፤የሰንደቅ ዓላማ፤ የወሰንና ማንነት፣ የታሪክ አረዳድ፤ የአሰተዳደር ሥርዓት፤በሕግ የበላይነት፣መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች ፣ኅብረ-ብሔራዊነት፣አብሮነት እና የሀገር ሉዓላዊነት ዋና ዋናዎቹ ናቸው ፡፡ በነዚህ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሁሉን አቀፍ ምክክርና ዉይይት በማድረግ መሰረታዊ መግባባት ላይ የደረሰ የፖለቲካ ማኅበረሰብ እውን ማድረግን እና መንግሥትና ህዝብን መግባባት ላይ እንዲደረሱ የሚያስችሉ ውይይቶችን በማካሄድ የዜጎችን የጋራ ፍላጎትና ተከባባሮ የመኖርን ባህል ሊያጎለብቱ የሚችል ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ሀገር በቀል ማኅበራዊ ሀብቶቻችንን እና እሴቶቻችንን በአግባቡ በመጠቀምና በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች መግባባት ላይ በመድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሰላም፤ለብሔራዊ መግባባትና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ግንባታ ማዋል እና በሂደቱም ለተግባራዊነቱ እንቅፋት የሆኑ አስተሳሰቦችና ተግባራትን በመለየት እርምት መስጠትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ!