በሀገራችን ስር ሰዶ የቆየውን የተረጅነትና የልመና አስተሳሰብ በማስወገድ ህዝቡን ወደ ላቀ ምርታማነት ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ
በሀገራችን ስር ሰዶ የቆየውን የተረጅነትና የልመና አስተሳሰብ በማስወገድ ህዝቡን ወደ ላቀ ምርታማነት ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ
ሰኔ 20/2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ''ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ክብር፣ ነፃነት እና ሉዓላዊነት'' በሚል ወቅታዊ ሀገራዊ አጀንዳ ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ላይ የሰላም ሚኒስቴር የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መብራቱ ካሣ ''ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሃገራዊ ክብር፣ ነፃነት እና ሉዓላዊነት '' የሚል ሰነድ አቅርበዋል።
የሰነዱ ዓላማ በሀገራችን ስር ሰዶ የቆየውን የተረጅነትና የልመና አስተሳሰብ በማስወገድ ህዝቡን ወደ ላቀ ምርታማነት ከፍ ማድረግ ነው ያሉት አቶ መብራቱ ከተረጅነት አስተሳሰብ በመላቀቅ እና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን በራስ አቅም ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ያደርጋል ብለዋል።
የውይይቱ ዓላማም ችግርን በራስ አቅም ለመፍታት የሚያስችል ሀገር በቀል ስርዓትን እና አቅምን በማጎልበት ዘላቂነትን ማረጋገጥ እና የፌዴራል ተቋማትን ሚና መለየት መሆኑን ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ ከተረጅነት መላቀቅ እና በራስ አቅም ኢኮኖሚን መምራት የሚለው ሃሳብ በፖሊሲ ደረጃ መምጣቱ ትልቅ ሀገራዊ ለውጥ /turning point/ ነው ብለዋል።
"በራስ አቅም መቆም እና ከተረጅነት መላቀቅ" የሚለውን ሃሳብ መሬት ላይ ለማውረድ ሁለት ነገሮች ያስፈልጉናል፣ እነዚህም አጠቃላይ የህዝቡ የአስተሳሰብ ለውጥ እና መረዳት ከፍ ማድረግ እና በፖሊሲው ላይ ሀገራዊ መግባባት ላይ መድረስ መሆኑን ገልፀዋል።
በቀረበው ሰነድ ላይ ከሰራተኞች ጥያቄዎችና ሃሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል።