ሀገር አቀፍ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ መርሐ ግብርን በሚመለከት መግለጫ ተሰጠ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመተባበር ‹‹በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ›› በሚል መሪ ሐሳብ  በሀገር አቀፍ ደረጃ በክረምቱ ወራት የሚከናወን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ መርሐ ግብርን አስመልክተው የሦስቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ 

የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና የብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)

ንቅናቄው ‹‹በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ›› በሚል መሪ ሐሳብ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ያስጀመሩት ሀገራዊ ንቅናቄ መሆኑን ገልጸው “ሀገርና ሕዝብ በዜጎች ነጻ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበት፤ ነባሩን የአብሮነትና የመደጋገፍ ባህላችንን የምናድስበት፤ ማኅበራዊ ግንኙነታችንን እና ብሔራዊ መግባባትን የምናጠናክርበት፣ ሀገርን በነጻ በማገልገል ከተለመደው ዓይነት አርበኝነት ለየት ያለ አርበኝነት የምንፈጽምበት፤ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ እና ልዩ የሆነ ንቅናቄ ነው” ብለዋል፡፡ 

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጦሽኔ “ለአብሮነት እሴት መሸርሸር ምክንያት የሚሆኑት አለመተዋወቅና አለመቀራረብ ስለሆነ በዚህ የክረምቱ በጎ ፈቃድ ሥራ የሚፈጠር መቀራረብና መተዋወቅ ሀገራዊ እሴትን ለመገንባት ጠቃሚ ነው”  በማለት ይህንንም ተፈጻሚ ለማድረግ ኢትዮጵያ ብዙ ወጣት ያላት ሀገር እንደመሆኗ ወጣቱን በስፋት ለማሳተፍ የተለመደው ዓይነት አሠራር ብቻ በቂ እንደማይሆን አስገንዝበው መሰል ንቅናቄዎችን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

ክብርት ወ/ሮ ሙና አህመድ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ “የበጎ ፈቃድ ሥራ በሀገራችን የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ቢሆንም ከለውጡ ወዲህ ባገኘው ልዩ ትኩረት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተጀምሮ ወደ ሥራ የተገባ እና በጠንካራ ድጋፍና ክትትል ለመምራትና በየደረጃው ያሉትን ባለድርሻ አካላት በሰፊው በማሳተፍ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚተገበር ሀገራዊ ፕሮግራም መሆን ያለበት ነው” ሲሉ አክለዋል፡፡  ንቅናቄው በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎችን ጨምሮ 40 ሚሊየን በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ ከ50 ሚሊዮን በላይ የማኅበረሰብ አካላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን በመግለጫው ተገልጿል፡፡ 

በክረምቱ ወራት በአረንጓዴ አሻራ፣ በቤት እድሳት፣ ለአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች ልዩ ልዩ ማኅበራዊ አገልግሎት በመስጠት፣ በትምህርትና በጤና ዘርፎች ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን በማገልገል ማኅበራዊ ትስስራቸውን የሚያጠናክሩበት መሆኑ ተነግሯል፡፡