ሀገራዊ ሰላምን በማጽናት ሂደት የሰላም እናቶች ሚና በሚል መሪ ቃል ምክክር ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሰላም እናቶች ማህበር ጋር በመተባበር በባህርዳር ከተማ ውይይት አካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት በኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ ወንድወሰን መኮንን የሰላም ሚኒስቴር የሰላም እናቶችን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየተንቀሳቀሱ የሚስተዋሉ ውጥረቶችን ለማርገብና የሰላም መልዕክተኛነት ሚናቸውን እንዲወጡ ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበር ገልፀዋል።

አቶ ወንድወሰን በንግግራቸው "ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በባሕል፣ በቋንቋና በፖለቲካ አመለካከት ሊለያዩ ይችላሉ፤ እንዲሁም የውስጥ ችግርም ሊያጋጥማቸው ይችላል፤ ነገር ግን የውጭ ጠላትና ወራሪ ኃይል ብሔራዊ ጥቅማችንና ሀገራዊ ክብራችንን ለመዳፈር ድንበር ተሻግሮ ሲመጣ ግን የውስጥ ችግራቸውን ወደ ጎን ትተው ሀገራዊ ክብርንና ሉአላዊነታችንን ደፍጥጦ የሚመጣን ወራሪ ኃይል በአንድነት ተመው እና በጋራ ተፋልመው ሉአላዊትና የተከበረች ሀገርን አስረክበውናል። ይህ ከቀደምት አባቶቻችን እናቶቻችን የወረስነው አኩሪ ታሪካችን ነው፡፡ ስለሆነም በዘመናት መካከል ፈተናዎችን በድል ስንሻገርና ለቀሪው ዓለም ትምህርት እየሰጠን የመጣነው በኢትዮጵያዊ ጀግንነት፣ አርበኝነት እና የአብሮነት ታሪካችን ነው፡፡

ካለፈው የጋራ ታሪካችን በመማር፣ የዛሬን ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ ለነገ የስኬታችን ምስጢር "ኢትዮጵያዊ አንድነታችን" መሆኑን ተረድተን በተለያዩ ምክንያቶች የሚያጋጥሙ ልዩነቶቻችንን በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት ያለበት መሆኑን ተገንዘበን የጋራ የሆነችውን ሀገራችንን በሰላም በልማት በዲሞክራሲ እና በሁለንተናዊ ብልጽግና አንገትዋን ቀና አድርጋ እንድትጓዝ ማድረግ ይገባናል"ብለዋል፡፡

ሀገራዊ የሰላም አደረጃጀቶቻችንን በማረታታት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ማህበረ-ባህላዊ አቅሞቻችንን ተጠቅመን በሰላማዊ አማራጮች ብቻ መፈታት እንዳለባቸው አስገንዘበዋል፡፡ በዚህም መሰረት የሰላም እናቶቻችን ሀገራዊ ሰላምን ለማጽናት ያላቸው ተፈጥሮአዊ ፀጋ በመጠቀም አዎንታዊ ተጽዕኖአቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሰላም እናቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መቅደስ እስጢፋኖስ በበኩላቸው ከሁሉም የሀገራችን ክልሎች የተውጣጡ 21 በጎፈቃደኛ የሰላም እናቶችን በማሰባሰብ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ ግጭቶችን ለማርገብና ሰላማዊ መንገዶችን ብቻ ታሳቢ ባደረገ መልኩ አለመግባባቶች እንዲፈቱ ጥረቶችን ሲያደርጉ እንደነበረ ጠቅሰው አሁንም በተቃርኖ ሁኔታ ወስጥ ያሉ ልጆቻችን ልዩነቶቻቸውን በመወያየት፣ በምክክር፣ በድርድር እና በሽምግልና መፍታት እንዳለባቸው እና ሀገራዊ ሰላሙ እንዲጸና እናታዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የምክክር መድረኩ ሀገራዊ ሰላምን ለማጽናት የሰላም እናቶች ሚና በሚል ርዕስ መነሻ ጽሑፍ በሰላም ግንባታ ባለሙያ በሆኑት በወ/ሮ ዜይኔባ ሱንከሞ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡