በአርብቶአደር/ከፊል አርብቶአደር አካባቢዎች ላይ የግጭት መንስኤዎችና መወሰድ የሚገቡ የመፍትሄ እርምጃዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ( ሰላም ሚኒስቴር ) የሰላም ሚኒስቴር የአርብቶአደር /ከፊል አርብቶአደር አካባቢዎች የግጭት መንስኤና መወሰድ የሚገቡ የመፍትሄ እርምጃዎች ላይ ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ባለሙያዎች፣ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ አርብቶአደሮች  ተገኝተዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አምባሳደር እሸቱ ደሴ የውይይቱ አላማ የሰላም ሚኒስቴር በዕቅድ የያዛቸውን ተግባራት ለማከናወን የሚያግዙ መረጃዎችን ለመሰበሰብና በክልሉ ያሉ አርብቶአደሮች በደረቅ እና እርጥበት ወቅቶች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች፤የችግሮቹን ምንጭ እና የመፍትሄ ሃሳቦችን በመለየት በጋራ ለመስራት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ 

በመሆኑም በዛሬው ውይይት በየአካባቢው ያሉ የግጭት መንስኤዎችን ለይቶ በማውጣት እና የመፍትሄ ሀሳቦችን በመለየት ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት በጋራ መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በመድረኩ ላይ በሰላም ሚኒሰቴር የግጭት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ይርጋለም መንግስቱ ሀገራዊ የግጭት ተለዋዋጭ ባህሪ እና ተጽህኖ እና የአርብቶ አደር አካባቢዎች በደረቅና ርጥበት ወቅት የሚታዩ ችግሮች፤ እንዲሁም የችግሮች ምንጭና የመፍትሄ ሀሳቦች በሚል ርዕስ የመወያያ ጹሁፍ አቅርበዋል፡፡