የጸጥታ ሴክተር የሥነ ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ፎረም ምስረታ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በሰላም ሚኒስቴር የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ስራ አስፈጻሚ አስተባባሪነት መጋቢት 02/2016 ዓ.ም የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ፎረም ምስረታ መደረጉን መነሻ በማድረግ፣

ግንቦት 17/2016 ዓ.ም በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሰላም ዘርፍ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ፎረም ምስረታ መደረጉን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ሴክተር የሥነ ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ፎረም ምስረታ ተካሄዷል።

በፎረሙ ምስረታው ላይ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስቴር የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ስራ አስፈፃሚ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት May be an image of 1 person, beard and suitአቶ አስቻለው ገብሬ የመድረኩ ዓላማ በየደረጃው ያለውን የጸጥታ ሴክተር የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ክፍሎች ትስስር ለማጠናከር ነው ብለዋል።

በጸጥታ ሴክተር የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች ፎረም ማንዋል የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ጉዳዮች ድጋፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ለማ ገቢሳ ቀርቧል።

በፕሮግራሙ ማጠቃለያም የሙስና መከላከል እቅድ ቀርቦ የጸጥታ ሴክተር የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ክትትል ስራ አስፈፃሚ ተመርጧል።May be an image of 5 people, people studying and text