የሰላም ሚኒስቴር ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የብዝሃነትና የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የምክክር መድረክ አካሄዷል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ግንቦት 6/2016 . የሰላም ሚኒስቴር ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የብዝሃነትና የህዝብ ግንኙነት /ቤት ጋር በመተባበር  ከክልል እና ዞን የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች ጋር የምክክር መድረክ  በአክሱም ከተማ  አካሄዷል፡፡

በምክክሩ የሰላም ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መብራቱ ካሳ ላለፉት ጥቂት ዓመታት አባቶቻችን በጥበብ ለዘመናት ያቆዩት የአብሮነትና የመቻቻል ታሪካችንን ጠብቀን ማቆየት ባለመቻላችን አላስፈላጊ ወደሆኑ ግጭቶች በመገባቱ በሀገራችን ህዝቦች መካከል  ያለመተማመን፣ የስጋትና የጥርጣሬ መንፈስ ተስተውሏል ይህ ያለመተማመን መንፈስ ተወግዶ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን በማጠናከር ሰላማችንና አብሮነታችን ቀድሞ ወደነበረው ሁኔታ እንዲመለስ ተከታታይ የሰላም ግንባታ ሥራ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀው  በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ግጭቶች ወደ ነበሩበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የኃይማኖት ተቋማት ያላቸው ሚና የጎላ ነው ብለዋል፡፡

አቶ መብራቱ ካሳ አክለውም ኃይማኖቶች ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን፣ ከመለያየት ይልቅ አንድነትን፣ከቂም በቀል ይልቅ ይቅርታን ማስቀደምን በመረዳት አሁን እያደረጋችሁ ካላችሁት አስተዋፆ ይበልጥ ዛሬ በምናካሂደው መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች የተሰሩ መልካም ስራዎችን ልምድ በመለዋወጥና እየገጠማችሁ ያሉትን ችግሮችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ጀምሮ በየደረጃው ላሉ የመንግስት አመራር እንዲያውቀው በማድረግ በመንግስትና በህዝብ መካከል ያላችሁን የድልድይነት ሚና ልትወጡ ይገባል በማለት ገልፀዋል፡፡

ሰላም ለሁሉም ፍጡራን  ዘራቸውና ህልውናቸው እንዲቀጥል የምታደርግ የምትናፈቅ ሀብት ናት ያሉት  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የብዝሃነትና የህዝብ ግንኙነት /ቤት ኃላፊ አቶ ካልአዩ አሰፋ የኃይማኖት ተቋማትም ሰላምን በመስበክ ሰላም ከሚያደፈርሱ ሁሉም ነገሮች ትውልዱ እንዲጠየፍና ትውልዱን በመገንባት የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል ፡፡

የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች የኃይማኖት አባቶች የክልልና የዞን የፀጥታ አመራሮችና ባለሙያዎች በምክክር መድረኩ ተሳትፈዋል፡፡