በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በመሰልጠን ላይ የሚገኙት 5ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት በጎ ፈቃደኛ ሰልጣኞች የበጎነት ተግባር እያከናወኑ ይገኛሉ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በመሰልጠን ላይ የሚገኙት 5ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት በጎ ፈቃደኛ ሰልጣኞች የበጎነት ተግባር እያከናወኑ ይገኛሉ።

በቅርቡ መደበኛ የጤና ተማሪዎችን ተቀብሎ ስራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ በሚገኘው በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ በመገኘት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጥተዋል።

በዚህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም ለተማሪዎች ምኝታ አገልግሎት የሚውሉ ተደራራቢ የብረት አልጋዎችን ወደ የተዘጋጀላቸው የተማሪዎቹ ምኝታ ክፍሎች ማስገባት፣ በጊዜያዊነት ለተለያዩ አገልግሎቶች ሲውሉ የነበሩ ልዩ ልዩ ቤቶች ፍርስራሽ እንጨቶችን ወደ አንድ ቦታ በመውሰድ የመከመርና መልክ የማስያዝ ስራ እና ደረቅ ቆሻሻዎችን አንድ ቦታ ላይ በመከመር የማቃጠል ስራዎች ተሰርተዋል።