ሀገሬን እገነባለሁ፣ ሀላፊነቴንም እወጣለሁ" በሚል መሪ ቃል በመላው ሀገሪቱ ከወጣቱ አደረጃጀቶች ጋር ሲካሄድ የቆየው ሀገራዊ የወጣቶች ንቅናቄ ማጠቃለያ ፕሮግራም ተጠናቀቀ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

"ሀገሬን እገነባለሁ፣ ሀላፊነቴንም እወጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ከመላው ሀገሪቱ ከተወጣጡ የወጣት አደረጃጀቶች ጋር በሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ ብሔራዊ ትርክት ግንባታ፣ በዘላቂ ሰላም ግንባታ የወጣቶች ሚና ላይ በማተኮር ሲካሄድ የቆየው ውይይት ተጠናቋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ በሰላም ሚኒስቴር የሀገር ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ዘላቂ ሰላምን፣ልማትንና ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ወጣቱ የማይተካ ሚና አለው ብለዋል።

ወጣቶች የሕዝቦችን አንድነት የሚሸረሽሩ ሀሰተኛ እና የጥላቻ መልዕክቶችን በመለየትና በመመከት እውነተኛ መረጃዎችን በመያዝ ለሰላም የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል ።

ወጣቱ በሁሉም ተቋማት ላይ ባለቤት እንዲሆን መንግስት እየሰራ መሆኑን ገልጸው ወጣቱም ለዚህ የሚሆን እውቀትና ክህሎትን ማዳበር እንዳለበትም አሳስበዋል።