በወሎ ዩኒቨርሲቲ 14ኛ ዙር የሰላም በጎ ፈቃድ ሰልጣኞች ለአቅም ደካሞች ድጋፍ አደረጉ
በወሎ ዩኒቨርሲቲ 14ኛ ዙር የሰላም በጎ ፈቃድ ሰልጣኞች ለአቅም ደካሞች ድጋፍ አደረጉ
በወሎ ዩኒቨርሲቲ 14ኛ ዙር ብሔራዊ የሰላም በጎ ፈቃድ ሰልጣኞች የሁለት ቀን የምግብ ወጫቸውን 160 ሺህ ብር በመቀነስ ለ190 ከስደት ተመልስሾች እና አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ዱቄት እርዳታ በማድረግ ወገንተኝነታቸውንና አብሮነታቸውን አሳይተዋል።
ሰልጣኞቹ በቆይታቸው ከስልጠናው ጎን ለጎን ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በመተባበርና በመቀናጀት የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችን በራሳቸው ተነሳሽነት ሲያበረክቱ የቆዩ ሲሆን ስልጠናውንአብሮአቸው እየተከታተለ ላለ አንድ የካንሰር ታማሚ ለሆነ ወጣት ገንዘብ በማሰባሰብ አብሮነታቸውን በተግባር አረጋግጠዋል።
በመሆኑም የበጎነት ለአብሮነት መልካም አርዓያነታቸው በግቢው መደበኛ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ያሉ ተማሪዎችንም አነሳስቶ አቅመ ደካሞችን ለመርዳት ባደረጉት እንቅስቃሴ እንዲቀላቀሉና እነሱም ገንዘብ በማዋጣት ለወገናቸው ደራሽ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የእርስ በእርስ ትስስራቸውንም አጠናክሮላቸዋል፡፡