በኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (KOICA) አዘጋጅነት ለሰላም ሚኒስቴር ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል
በኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (KOICA) አዘጋጅነት ለሰላም ሚኒስቴር ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል
ግንቦት 11/2017 ዓ.ም(ሰላም ሚኒስቴር) የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (KOICA) ለሰላም ሚኒስቴር ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የአቅም ግንባታ ስልጠናው ዓላማ የተቋሙን ሰራተኞች አስተዳደራዊ አቅምን በማጎልበት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለመገንባት ነው፡፡
ስልጠናው በክልል የሚከሰቱ ግጭቶችን ለመቆጣጠር እና የግጭት ቀውሶች እና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህዝቦችን የስነ-ልቦና ድጋፍ በማድረግ የኢትዮጵያን ማህበራዊ ካፒታል ለማሳደግ የሚያግዝ ነው ተብሏል ።
ስልጠናው በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን ከግንቦት 11 እስከ ግንቦት 22/2017ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።