የአፋር እና ሱማሌ ክልል ርዕስ መስተዳድሮች በተገኙበት በጅግጅጋ የኢፍጣር መርሐ ግብር ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ምሽቱን የአፋር እና ሶማሊ ወንድማማች ህዝቦች ታላቅ የጋራ የኢፍጣር መርሐ ግብር በጅግጅጋ አካሄዱ።

መርሀ ግብሩ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈጠረውን ሰላም በማፅናት የህዝብ ለህዝብ ትስስሩን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ላይ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማስቆምና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል ስምምነት መካሄዱ ይታወሳል።

ስምምነቱን ተከትሎ የሁለቱን ህዝቦች የግጭት ምክንያቶች በመለየት መፍትሄ ለማስቀመጥና ሰላምን ለማፅናት የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑም ቆይተዋል።

በዛሬው ዕለትም የጋራ የአፍጥር መርሀ ግብሩ የአፋር እና ሶማሊ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላም ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ ኢድሪስ፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በጅግጅጋ እየተካሄደ ይገኛል።