የተቋማት ትብብርና ቅንጅት ለአሰባሳቢ ትርክትና አዎንታዊ ሰላም ግንባታ ስኬት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ
የተቋማት ትብብርና ቅንጅት ለአሰባሳቢ ትርክትና አዎንታዊ ሰላም ግንባታ ስኬት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ
የካቲት 30/2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) የሰላም ሚኒስቴር ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልገሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች የብሄራዊነት ትርክትን ከመገንባት አንፃር የሚዲያዎች ሚና በሚል ስልጠና ሰጥቷል። የሰላም ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) የተቋማት ትብብርና ቅንጅትን በማጎልበት በተለይም ከሚዲያ ተቋማት ጋር አብሮ በመስራት ለሁለንተናዊ ሰላም እና ለሀገር ግንባታ አቅምንና እውቀትን አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ በሰፊው ለስልጠናው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

የሰላም ሚኒስቴር የተሰጠውን ተልዕኮ መሠረት በማድረግ በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እና ህብረ ብሄራዊ አንድነት እንዲጎለብት የተለያዩ የምክክር እና የስልጠና መድረኮችን የማመቻቸትና ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናቶች የማድረግ ስልቶች ላይ ተመስርቶ እየሰራ መሆኑን አንስተው ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ ለሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አመራርና ባለሙያዎች ግንዛቤ መፍጠር ጠቀሜታው እጅግ የጎላ በመሆኑ ስልጠናው መሰጠቱን የጠቀሱት ሲሆን ሰልጣኞችም አውቀው በማሳወቅ ሚዲያው የራሱን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ያደርጉ ዘንድ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በማሳሰብ ህብረ-ብሄራዊ ገዢ ትርክትን መገንባት የሁሉንም ጥረትና ተሳትፎ ይጠይቃል ብለዋል።
የስልጠና መድረኩ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልገሎት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ከሁሉም ክልሎች፣ 
ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እና ከፌዴራል ተቋማት የኮሙኒኬሽን እና የሚዲያ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።
ሰላም ለኢትዮጵያ!