የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከተባባሩት መንግስታት ልማት ፕርግራም /UNDP/ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከተባባሩት መንግስታት ልማት ፕርግራም /UNDP/ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
የካቲት 27/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ ከተባባሩት መንግስታት ልማት ፕርግራም /UNDP/ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሰላም ግንባታ ሥራዎችን መሠረት አድርገው ውይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይታቸውም የሰላም ሚኒስቴር እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራት በተለይም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ብሔራዊ መግባባትን ለማጎልበት እና መሰረታዊ የሀገር መንግስት ግንባታ ሥራዎች እንዲጠናከሩ ለማድረግ የሚያስችሉ የተከናወኑ ስራዎችን አስመልክቶ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ልማት ድርጅት ተወካይ ሚስተር ሳሙኤል ዱይ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃ አመስግነው በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ቀልጸዋል። ቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለመደገፍ የጋራ ቴክኒካል ቡድን አቋቁመው አብሮ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡