በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ‹‹ብሄራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጣናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የህዝቦች ተጠቃሚነት›› በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የሀገር በቀል እውቀቶች ማስተባበረያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዱኛ መኮንን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ለዘላቂ ብሄራዊ ጥቅሞችና የሀገር ግንባታን በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና እንዳላቸው በማወቅ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

May be an image of 1 person and textየመወያያ ጽሁፍ በዩኒቨርሲቲው የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህረት ክፍል ኃላፊ መምህርና ተመራማሪ በሆኑት መምህር ኃይሌ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ጽሁፍ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል::

May be an image of 4 people and daisየሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክና ምርምር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፀጋዬ ደዩ በውይይቱ መዝጊያ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር ሀገራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ፣ የአካባቢውን ግንኙነትን ለማጠናከር እና የህዝብን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ብሎም በትብብር ለመስራት የሁሉም አካላት ድርሻ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ምሁራን በሀገር አቀፍ የውይይት መድረኮች እና ሌሎች መሰል ፕሮራሞች ላይ በመሳተፍ እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በማካፈል ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የውይይት መድረኩ የሰላም ሚኒስቴር ከሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣ ምሁራን፣ ተማሪዎች፣ የሰሜን ሸዋ ዞንና የፍቼ ከተማ አሰተዳደር ጽ /ቤት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ምንጭ፡- የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ