ምክር ቤቶቻችን ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታችን በሚል ርዕስ ምክክር ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የካቲት 4/2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና አባላት፣ ከፌዴሬሽን ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊዎች ፣ ከክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ም/አፈ-ጉባኤዎች ጋር “ምክር ቤቶቻችን ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታችን’’ በሚል መሪ ሐሳብ ምክክር ተካሂዷል።

በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር፣ አዎንታዊ ሰላምን ለመገንባት፣ የሀገር ብሔርና እና ሀገረ መንግሥት ግንባታውን በአስተማማኝ ደረጃ ለማከናወን በተጀመረው ጉዞ በጎ ተጽእኖ ከሚያሳርፉ አጋር አካላት ጋር በትብብር መሥራት የሚጠበቀውን ውጤት የተሟላ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡

“ሀገር በጠንካራ መሠረት ላይ የሚገነባው ጠንካራ ተቋማት ሲገነቡ፤ ተቋማትም ተልዕኮዎቻቸውን በትጋት ሲፈጽሙ ነው” ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለብሔራዊ መግባባትና አንድነት መጠናከር ምክር ቤቶች ተቀናጅተው በአጋርነት መሥራት እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡

ክቡር ሚኒስቴር ዴኤታው የጋራ ሰላማችንን የሚያናጋውን እና በዜጎች መካከል ጥርጣሬ የሚፈጥረውን ነጠላ ትርክት፡- የጋራ ማነታችን በሆነው ኢትዮጵያዊነት የሚያሰባስብ የጋራ ትርክት መተካት፤ እንዲሁም የተጀመሩትን የዘላቂ ሰላም ግንባታ ሥራዎች ከፍ ማድረግ የሁሉንም ትኩረት እና ትብብር የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ የተከበሩ ሎሚ በዶ በበኩላቸው “ኢትዮጵያ በብዝኃነት የተገነባ አንድነትን ጠብቃ፣ ፈርጀ-ብዙ ፈተናዎችን ተሻግራ፣ ነፃነቷን አስጠብቃ የኖረች የረጅም ታሪክ ባለቤት እንደመሆኗ መጠን ከሀገረ መንግሥት እና ብሔረ መንግሥት ግንባታ አንፃር ያልተሠሩ ሥራዎች በበቂ ሁኔታ እንዲሠሩ ሁሉም አስተዋፅኦ ሊያበረክት ይገባል”፤ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

በምክክሩ አብሮነትን እና አንድነትን የሚያጠናክሩ ሀገራዊ እሴቶችን በማጎልበት፣ ችግሮች ተቀርፈው ለቀጣይ ትውልድ ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር ለማስተላልፍ የተጀመረውን የሀገረ መንግሥት እና ብሄረ መንግሥት ግንባታ እንዲሁም የዘላቂ ሰላም ግንባታ ሥራዎች በላቀ ደረጃ ተፈፃሚ እንዲሆኑ ስልቶችን በጋራ መቀየስና በአጋርነት ተቀናጅቶ በመተግበር የምክር ቤት አባላቱ ወደ ማህበረሰቡ ወርደው ግንዛቤ ለመፍጠር መግባባት ላይ ተደርሷል።

በምክክር መድረኩ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት አስመልክቶ የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ በሆኑት አቶ አዱኛ በቀለ እንዲሁም " ምክር ቤቶቻችን ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታችን" በሚል ርዕስ በዶክተር ሮባ ጴጥሮስ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።