ለቅንጅታዊ ሥራ የመግባቢያ ስምምነት ተፈጸመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ከኢፌዴሪ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጋር ተልዕኳቸውን ማዕከል ባደረጉ የጋራ ጉዳዮች በቅንጅት ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። የመግባቢያ ስምምነቱን የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ቸሩጌታ እና የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ተፈራርመዋል ።

መግባቢያ ስምምነቱ የተደረገው ግጭትን በሰላም ለመፍታት በተደረገ የሰላም ስምምነት መሠረት ከተዋጊነት የተሰናበቱ የቀድሞ ተዋጊዎች የሲቨክ ሥልጠና አግኝተው፣ የሰላም ሐሳብ ይዘው፤ ከማኅበረሰብ ጋር በዘላቂነት እንዲቀላቀሉ እና ሰላማዊ የሲቪል ሕይወት መምራት እንዲችሉ ሁለቱ ተቋማት በትብብር መሥራት እንዲችሉ የሚያግዝ እና የተቋማት ጥምረት የመፍጠር መሰረት ነው፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ !