በሰላም ግንባታ ሂደት የሚከናወኑ ተግባራትን እንደግፋለን - የተባበሩት መንግስታት የተለያዩ ድርጅቶች

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ነሃሴ 22 ቀን 2016 . መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ስራዎችን መደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከሰላም ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተወያዩ።

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ  ሚኒስትር ዴዔታ / ከይረዲን ተዘራ በውይይቱ ወቅት እንዳሉት መንግስት ዘላቂና አዎንታዊ ሰላምን በሀገሪቱ ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን በማዘጋጀት ወደ ተግባር መግባቱን ገልፀው በሀገሪቱ  የውይይት ባህልን ለማጎልበትና በተለይ ወጣቱ የሰላም ባለቤት እንዲሆን የሚያስችሉ የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ስራ ተግባራትን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በስፋት እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።የሰላም ግንባታ ስራ የበርካታ አካላትን ቅንጅትን እንደሚፈልግ በመግለፅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ጋር በትብብር  እንዲሰሩ / ዴዔታው ጠይቀዋል።

በሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ቸሩጌታ ገነነ በበኩላቸው ግጭቶች በሰላማዊና በዘላቂነት እንዲፈቱና መላው ህዝብ በመከባበርና  በመተባበር እንዲሰራ ለማስቻል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀው ባለፉት 11 ወራት 700 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያቸው እንዲመለሱና ከህብሰተሰቡ ጋር በሰላማዊ መንገድ እንዲቀላቀሉ መደረጉን ተናግረዋል።

በወይይቱ መድረኩ የተገኙ በተባበሩት መንግስታት ስር  ያሉ  ድርጅቶች በበኩላቸው መንግስት ሀገሪቱን የተረጋጋችና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ እያከናወነ ያላቸውን የሀገራዊ ምክክር፣የሽግግር ፍትህ እና የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ተግባራትን አድንቀው ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የሚያከናውናቸውን የሰላም ግንባታና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የመመለስ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ቃል ገብተዋል።በውይይቱ የተባበሩት መንግስታት የምስራቅ አፍሪካ ኃላፊ፣ ዩኤንዲፒ እንዲሁም በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ / ራሚስ አልካሮፍን ጨምሮ በርካታ ድርጅቶች ተሳትፈዋል።