የሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊነት ጉዳይ አስተባባሪ ጋር ውይይት አደረገ
የሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊነት ጉዳይ አስተባባሪ ጋር ውይይት አደረገ
የሰላም ሚኒስቴር በሰላም ግንባታ በትብብር መሥራት በሚቻልበት ጉዳይ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊነት ጉዳይ አስተባባሪ ጋር ውይይት አደረገ
ነሐሴ 14 ቀን 2016ዓ.ም. የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊነት ጉዳይ አስተባባሪ ዶ/ር ራሚስ አልካብሮቭ ጋር የሰላም ግንባታ ሥራዎችን በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ዘላቂ የሆነ አዎንታዊ የሰላም ግንባታ ሥራ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ባህሪ ያለው በመሆኑ ከተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በትብብር መሥራት የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸው ለዚህም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊነት ጉዳዮች አስተባባሪ ዶ/ር ራሚስ አልካብሮቭ አጠቃላይ አዎንታዊ ሰላምን ለመገንባት ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎትና በማኅበረሰብ ውይይት ላይ እየተሠሩ ያሉትን ሥራዎች አደንቀው ተቋሙ የሚያከናውናቸውን ሁለንተናዊ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ሥራ እንደሚደግፉና ለውጤታማነቱም ሌሎች የዓለም አቀፍ ተቋማትን ጭምር ለማስተባበር ቃል ገብተዋል፡፡