የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር አካሂደዋል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሐምሌ 22 ቀን 2016 . የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ሀሳብ በሲዳማ ክልል ዳሌ ወረዳ የችግኝ ተከላ  መርሐ-ግብር አካሄደዋል፡፡

በመርሐ-ግብሩ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር  ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ"በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በመላው ሀገራችን እየተካሄደ እንደሆነ ገልፀው የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞችም ሲዳማ ክልል ዳሌ  ወረዳ በመገኘት የችግኝ ተከላ አካሂደናል ብለዋል፡፡ አክለውም የሲዳማ ክልል ሰላም የሰፈነበትና ሰላማዊ ክልል በመሆኑ እዚህ ክልል ላይ የምንተክለው ችግኝ ብቻ ሳይሆን የሲዳማ ክልል አሁናዊ ሰላም የበለጠ እንዲፀና እና ዘላቂ እንዲሆን ሰላምን ለማፅናትና ለመትከል  በጋራ ለመስራት ያለመ  ነው ብለዋል፡፡

የሰላም እጦት በሰው ሰራሽ ችግሮች ብቻ ሳይሆን በተፈጥሮ አደጋዎች ጭምር የሚከሰት ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ በተለይም ደግሞ በዚህ ዓመት በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን እና በሲዳማ ክልል ወንሾ ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ዜጎቻችንን አጥተናል ፡፡ ይህ ሰላማችንን እያሳጣን ዜጎቻችንን እየነጠቀን ያለው የተፈጥሮ አደጋ በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ  የተራቆቱ አካባቢዎችን በደን በመሸፈን አካባቢያን መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ  ኃላፊ  አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በበኩላቸው በሁሉም  የሀገራችን ክፍሎች ከችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ጎን ለጎን ሀገራዊ አንድነትን ለመፍጠር  የሰላም ግንባታ ስራዎችን በጋራ መስራትና የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርና ሰራተኞች፣ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የብሔራዊ በጎፈቃድ አገልግሎት በጎፈቃደኛ ወጣቶች እና የማህበረሰብ ክፍሎች በችግኝ ተከላው ተሳትፈዋል፡፡