የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አሜሪካ በሚገኘው ዩተሃ ግዛት የቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታ ተረከበች ሀገራዊ የግጭት ክስተቶች ፣መንስኤዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች "ላይ የተካሄደ ጥናት ውጤት ይፋ ተደረገ
Publicador de continguts
ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አሜሪካ በሚገኘው ዩተሃ ግዛት የቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታ ተረክባለች።
ቦታውን አሜሪካ የሚገኘው የኋለኛው ቀን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን (Church of Jesus Christ of Latter-day Saints (LDS),) ያበረከተ ሲሆን የስተርሊንግ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ተብሏል።
የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በርክክብ ስነ ስርዓት ወቅት እንደተናገሩት የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች አሜሪካ በሚገኘው ዩተሃ ግዛት ለስራ በሄድንበት ወቅት በግዛቱ የሚገኙ የኦርቶዶክስ አምነት ተከታይ ምዕመናን የማምለኪያ ቦታ የሚሆን ቤተክርስቲያን ባለማግኘታቸው ሲቸገሩ ማስተዋለቸውን ገልፀው ችግሩን ለመፍታት የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በጋራ ባደረጉት ጥረት ቦታው እንዲገኝ ሆኗል ብለዋል።
መንግስት ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅርርብ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ምዕመናን ሃይማኖታቸውን በነፃነት እንዲያራምዱ እና በሃይማኖቶች መካከል የአብሮነት እና የትብብር መንፈስ እንዲያድግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን (Church of Jesus Christ of Latter-day Saints (LDS),) የቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታውን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማስረከቡ በሐይማኖቶች መካከል ያለውን የመደጋገፍ ፣የአብሮነት እና የትብብር መንፈስ ያሳያል ያሉ ሲሆን ይህ ደግሞ የኢትዮጵያውያን ዕሴት ሆኖ ለዘመናት ቆይቷል ብለዋል።
መንግስት ዜጋ ተኮር የሆነ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ሚኒስትር ዴዔታው ከዚህ የወሰድነው ትምህርት አንዱ ሃይማኖት አንዱን መደገፍ ከቻለ እና በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መተባበር ከቻሉ ሀገር ሰላሟ እንደሚፀና ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አሜሪካ በሚገኘው ዩተሃ ግዛት የቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታ በማግኘቷ ታላቅ ደስታ ይሰማናል ፣በሂደቱ ድጋፍ እና ትብብር ለአደረጉ ሁሉ ምስጋናዬ ላቅ ያለነው ብለዋል።
Continguts més visitats
ኅዳር 23/2016 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ "ሀገራዊ የግጭት ክስተቶች ፣መንስኤዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች "ላይ የተካሄደ ጥናት ውጤት ይፋ የማድረግ መርሃ -ግብር ተካሄዷል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ታዬ ደንደአ በሀገራችን ከ2010 ዓ.ም እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ክልሎች በተለያዩ ምክንያቶችና የግጭት መንስኤዎች የሚከሰቱ ግጭቶች ወደ ሁከትን እና ብጥብጥ አድገው ከፍተኛ ጉዳት በሰውና በንብረት ሲያደርሱ ቆይተዋል፤ እያደረሱም ነው ብለዋል፡፡
የሰላም ሚኒስቴር እነዚህ የሚስተዋሉ ግጭቶችንና አለመግባባቶችን ለመፍታት በተናጠል ከመስራት ማህበረሰባዊ ለውጥ ሊያመጣ በሚያስችል መንገድ ሁሉንም ዜጎችና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ጥናቶችን ሲያካሂድ ቆይቷል በማለት ክቡር ሚኒስትር ደኤታው ገልፀዋል ፡፡
አክለውም በዛሬው ዕለት ይፋ የሚደረገው ጥናት ዋና ዓላማ እና አስፈላጊነት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ ግጭቶች መንስዔዎቻቸውን በመለየት፤ በቴክኖሎጂ የታገዘ የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ስርዓትን በመዘርጋት ግጭቶችን ከመከሰታቸው በፊት መከላከል፣የህብረተሰቡን በሰላም የመኖር ልምድ በመጠቀም እና የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት የዘላቂ መፍትሄ አማራጮችን መጠቆም ነው ብለዋል ፡፡
''ሀገራዊ የግጭት ክስተቶች ፣መንስኤዎችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች'' በሚል ርዕስ ጥናት ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጰያ ጥናትና ምርምር ተቋም ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የምርምር ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ አምሳሉ ናቸው።
ዶ/ር ደሳለኝ በጥናታቸው በኢትዮጵያ (ከ2018-2022 እ.ኤ.አ) የተከሰቱ ግጭቶች መንስኤዎችና የመፍትሄ ሃሳቦችን በዝርዝር አስቀምጠዋል።
ጥናቱ በኢትዮጵያ የተነሱ ግጭቶች በየትኞቹ የሀገራችን ክፍሎች በብዛት ተስተዋል የሚለውን የሚያሳይ የግጭት ፍኖተ ካርታ/conflict mapping/ የያዘ ሲሆን የተከሰቱ ግጭቶች መሰረታዊ እና አባባሽ ምክንያቶችን እና ምን ቢደረግ ግጭቶች ሊቀንሱ ይችላሉ ሚለውን ሃሳብ አስቀምጧል።
በሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ስዩም መስፍን የሰላም ሚኒስቴር በተሰጠው ስልጣን መሰረት ግጭቶች መንስኤዎችን አጥንቶ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በጥናት ለይቶ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ ገልፀው ዛሬ ይፋ የተደረገው ጥናት ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት በጋር በመሆን የተካሄደ እንደሆነ እና ከትግራይ ክልል በስተቀር ጥናቱ ሁሉንም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ያካተተ መሆንንአስገንዝበዋል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሰላምና የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና የኮሚቴ አባላት ፣የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ፣የፌዴራልና የክልል የመንግስት ተቋማት ኃላፊዎች እና የባለድርሻ አካላት አመራሮች በፕሮግራሙ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡