ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ከሚገኘው ከመሐመድ ቢን ዛይድ ፎር ሁማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር  ያዘጋጁት ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡

የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ክቡር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ፣ በጉባዔው መክፈቻ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር “መድረኩ ቀጣይ የሆኑ ሰፋፊ ዓለም አቀፍ መድረኮችን ለማዘጋጀት መሠረት የሚጥል ታላቅ ጉበዔ ነው” ብለዋል፡፡ ክቡር ፕሬዝዳንቱ   የሃይማኖት ተቋማት የመቻቻል፣ አብሮ የመኖርና የመተሳሰብ እሴቶችን እና ማኅበራዊ ትስስሮችን በማጠናከር በሰላም ግንባታው ላይ ሚናቸው እንዲወጡም መልእክት አስተላልፈዋል።

የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባቀረቡት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር  ኢትዮጵያ ቀደምት እና ጥንታዊ ብዝኃ ሀይማኖቶች ያሉባት ሀገር መሆኗን ገልጸው “ጉባዔው 99 በመቶ ሕዝባችን በየሃይማኖቱ አማኝ በሆነው ሀገራችን ይህ ታላቅ እና ታሪካዊ ጉባዔ መዘጋጀቱ የሚመጥነን ብቻ ሳይሆን ብዙ ጥቅሞች ያሉት ነው” ብለዋል፡፡ 

የመሐመድ ቢን ዛይድ ፎር ሁማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ቻንሲለር ካሊፋ ሙባሪክ አሊ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ሀይማኖቶች በሰላም ተከባብረው የሚኖሩበት ሀገር በመሆኗ፤ ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆን መልካም ተሞክሮ ያላት ሀገር በመሆኑ ጉባዔው በኢትዮጵያ በመዘጋጀቱ እና የዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ ጉባዔ አካል በመሆናቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡