የሰላም ሚኒስቴር ለሰራተኞቹ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር በተቋማዊ ስነ-ምግባር እና መልካም አስተዳደር ፣ ተቋሙ እያከናወናቸው ባሉ ተግባራት እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ለሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠና መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ አዱኛ በቀለ ስልጠናው የተቋሙን ተግባርና ተልዕኮ በደንብ ተረድቶ እና ለተግባራዊነቱ የራሱን አሻራ የሚያሳርፍ አመራርና ሰራተኛ ለመገንባት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል ።

የምንሰራቸው ስራዎች ሁሉ በዕውቀት እና በስነ ምግባር ሊደገፉ ይገባል ያሉት አቶ አዱኛ ተቋሙ እያከናወናቸው ባሉ ተግባራት ላይ ሁሉም ሰራተኛ ሚና አለው ያሉ ሲሆን ተቋም የሚያድገው በአንድነት መንፈስ መስራት ስንችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

May be an image of 1 personበስልጠና መድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስቴር የሰው ሀብት ባለሙያ የሆኑት አቶ እሱባለው አልማው ‘’ሥነ -ምግባር እና ሙያዊ ሥነ- ምግባር” በሚል ርዕስ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ከስልጠናው በኋላም ጥያቄዎች እና ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጓል፡፡May be an image of 2 people, lighting, table, dais and text

May be an image of 1 person and newsroomበስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መብራቱ ካሣ በስልጠናው ያገኘናቸውን ዕውቀቶችና ክህሎቶች ወደ ተግባር በመቀየር ለተቋሙ ውጤታማነት መስራት ይገባናል ብለዋል፡፡ አክለውም የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ጊዜው የሚጠይቀውን የቴክኖሎጅ እና አለማቀፋዊ ሁኔታውን በመረዳት በስነ ምግባርና በታማኝነት ለአዳዲስ አሰራሮች ራስን ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል።

ሰራተኛው ያለበትን ችግር ለመፍታት እና የተሻለ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረግን እንገኛለን ያሉት ደግሞ የሰላም ሚኒስቴር የብቃትና ሰው ሀብት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብዙነህ ምክሩ ናቸው። አቶ ብዙነህ ሰራተኛው ህዝብን ለማገልገል ውል የገባ መሆኑን አውቆ በስነ-ምግባር እና በታማኝነት የተቋማችን ተልዕኮ ልናሳካ ይገባል ብለዋል።