የሰላም ሚኒስቴር በ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሐምሌ 17 ቀን 2017ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር) ፤ የሰላም ሚኒስቴር በ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ ዕቅድ የውይይት አድርገዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ ቀደም ካስመዘገብናቸው ዕድገት በላይ የሕዝባችንን ፍላጎት ማሟላት የሚችል ዕድገት ለማምጣት እንሠራለን፡፡ ካለፉት ጊዜያት አፈፃፀሞቻችን ልምድ ወስደን፤ በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፎች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የምንሰራበት የዕቅድ ዓመት እንደሚሆን ገልፀዋለዋል።

የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሁኔታዎችን እና አዝማሚያዎችን ያገናዘበ መርህ ተከትለን የተመዘገበውን የኢኮኖሚ እድገት አጠናክሮ የሚያስቀጥል ፕሮጀክቶችን ቀርጾ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን አስፍቶ እንደሚሠራ አሳውቀው የበጀት ዓመቱ ዕቅድ ስኬታማ እንዲሆን ተቋሙ በተሰጠው ኃላፊነትና ተግባራት ላይ መሠረት ባደረገ መልኩ ከሀገራዊ ዕቅድ ተመሳሳይ አቅጣጫ መሄድ፤ ሀገሪቱ ከምትሄድበት ፍጥነት ጋር ተመጣጣኝ እርምጃ በመጓዝ ጠንክረን መሥራት ይገባል ሲሉም ክቡር ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለ2018 በጀት ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ በየዘርፍ ዘርፉ ተለይቶ የታቀደውን ሀገራዊ ዕቅድ በጽሑፍ ያቀረቡት የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ እና የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ የሆኑት አቶ ሰውነት ቸኮል ሀገራዊ ዕቅዱ ያተኮረባቸው ዋና ዋና ነጥቦች በኢኮኖሚ ልማት፣ በመሠረተ ልማት፣ በእንዱስትሪ፣ በሰላም፣ በዴሞክራሲ፣ በፍትህ፣ በዲፕሎማሲ እና በሌሎችም እንደ ሀገር ትኩረት የደረገባቸውን ዋና ዋና ነጥቦች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

በዘላቂ ሰላም ግንባታው በማኅበረሰብ ውስጥ አዎንታዊ ሰላም መገንባት፣ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ማጎልበት፣ ግጭቶችን መከላከል መፍታት፣ ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ከዘመናዊ ሕግና ሥርዓት ጋር አስተሳስሮ ጥቅም ላይ ማዋል፣ የሰላም ብሔራዊ በጎ ፈቃድ ሥራዎችን ማጠናከር፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ተቋማት ማህበረሰባዊ ትስስሮችን ማጠናከርቋ ሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የሰላም ንቅናቄ ሥራዎች ማከናወን ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች መሆኑ በዕቅዱ ላይ ተመላክቷል፡፡

ዕድገቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሁሉም ዘርፎች የሚተገበሩ ተግባራትን በዝርዝር በመመልከት የሚኒስቴሩ ሠራተኞችና አመራሮች በጥልቀት ተወያይተው ሀገራዊ ዕቅዱ ተግባራዊ እንዲሆን ድርሻቸውን ለማበርከት እንደሚሠሩ ተወያይተዋል፡፡