ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከበረ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

መጋቢት 3/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር)፣ የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ49ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 114ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ “ፈጣን እና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል “ በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል።

በበዓሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ አንድ ማህበረሰብ ሚዛኑን ጠብቆ ማደግ የሚችለው ሴቶችን ማካተት እና ማሳተፍ ሲችል መሆኑን ገልፀው ሴቶች ሀገር በመገንባት ሂደት ውስጥ ትልቅ አቅሞ እንዳላቸው ማመን እና ለተግባራዊነቱ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

አሁን ለደረስንበት ሁኔታ ያለ ሴቶች ተሳትፎ አልደረስንም ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ የሰላም ሚኒስቴር ሴቶች በተፈጥሮ ለሰላም ቅርብ መሆናቸውን በመረዳት ሴቶች ላይ ትኩረት አድርገን እየሰራን እንገኛለን፤ በቀጣይም አጠናክረን እንሰራለን ብለዋል።

ሴቶችን በተለያዩ መዋቅሮች ማሳተፍ ሚዛኑን የጠበቀ ውሳኔ ለማሳለፍ ይረዳል ያሉት ክቡር አቶ መሐመድ በቀጣይ ሴቶችን ወደ አመራር ለማምጣት እና አቅማቸው እንዲጎለብት ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል ።

የሰላም ሚኒስቴር የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ወጋየሁ ቢያድግልኝ በበኩላቸው የሴቶችን አቅም የሚያሳደጉ እና የአመራር ብቃታቸውን የሚጨምሩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልፀው በቀጣይ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

አምባሳደር ታደለች ኃ/ሚካኤል እና የሰላም ሚኒስቴር የቀድሞ ባልደረባ የነበሩት እና በጦረታ የተሰናበቱት ወ/ሮ ሂሩት ዴሊቦ በበዓሉ ላይ ተገኝተው ተሞክሮአቸውን በዝርዝር አካፍለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር መካከለኛ አመራሮች ሴቶችን እድል ከመስጠት እና አቅማቸውን ከማከናወን አኳያ ያከናወኗቸውን ተግባራት እና የቀጣይ ዕቅዳቸውን አብራርተዋል።