ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ሥርዓቶችን ለማዳበር የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደረገ
ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ሥርዓቶችን ለማዳበር የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደረገ
ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ሥርዓቶችን ለማዳበር የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደረገ
ኅዳር 6/2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር)፣ ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ሥርዓቶች ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያከናወኑትን በጎ ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጓል፡፡
ኅዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር፣ ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ሥርዓቶች ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያከናወኑትን በጎ ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጓል፡፡
የሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት በማኅበረሰቦች ውስጥ ያሉ የእርቀ ሰላም ሥርዓቶቻችን ኢትዮጵያዊያን በብዙ ዘመናት የገነቧቸው ስለሆነ በማኅበረሰብ ውስጥ ተቀባይነት ያላቸው እና የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመፍታት ብቻ ሳይሆን ለመከላከልም ያለቸው አቅም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሥርዓቶቹ ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደርጉት ጥረቶች ስኬታማ ለማድርግ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የግጭት አመላካች ሁኔታዎችን አጥንቶ ሳይከሰቱ ማምከን እና የተከሰቱ ግጭቶችንም በዘላቂነት መፍታት እንዲቻል ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ሥርዓቶች እያከናወኑ ያሉትን በጎ ሚናዎች እንዲያጠናክሩ ለማገዝ የተለያዩ አጋር አካላት በተቀናጀ ትኩረት የሚሠሩ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ግጭት መነሻው አካባቢያዊ፣ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መነሻዎች ያሉት በመሆኑ በነዚህ መነሻዎች መሠረት አድርጎ የሚፈጠሩትን መረጃ ሰብስቦ ቀድሞ ለመከላከል የሚሆኑ ግብዓቶችን መሰብሰብና የግጭት አመላካቾችን ለማጥራት የሚሆን የዳታ ማዕከል ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን፤ ተግባራዊ ለማድረግም ከአጋሮች ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የጀስቲስ ፎር ኦል ፒኤፍ የፕሬዚደንት አማካሪ የሆኑት አቶ ውብሸት ክብሩ በበኩላቸው ጀስቲስ ፎር ኦል ፒኤፍ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የግጭት መከላከል ሥራዎችን ለመደገፍ እና የፍትህ ሥርዓቱ እንዲቃና ለማድረግ ለፀጥታ አካላትና የፍትህ ተቋማት ጥናት ላይ መሠረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በመሥራት ላይ መሆኑን ጠቅሰው የግጭት መረጃ ዳታ መሰባሰቢያና ማበልፀጊያ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
ውይይቱ ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ሥርዓቶች የሚያከናውኑትን ተግባራት ውጤታማነት ለማሳደግ፤ የባለድርሻ አካላትን ድጋፍ የሚያጠናከር ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የሰላም ሚኒስቴር ከጀስቲስ ፎር ኦል ፒ ኤፍ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው።