የሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር እና ከጀርመን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰብዓዊ ድጋፍ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች ጋር ውይይት አደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር እና የጀርመን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰብዓዊ ድጋፍ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለውን ዘርፈ ብዙ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን በማጠናከር በሀገራቱ መካከል የሚኖረውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እና የሰብዓዊ ድጋፎችን ለማጠናከር አብሮ መሥራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡May be an image of 1 person and newsroom

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ኢትዮጵያና ጀርመን የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላቸው ሀገሮች መሆናቸውን ገልጸው፤ ግንኙነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሚያከናውናቸው የሰላም ግንባታ ሥራዎች በጥልቀት አብራርተው የጀርመን ድጋፍና አጋርነት እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

May be an image of 1 personበኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ጀን ሄንፊልድ እና ልዑካኑ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች እንዲሁም ሀገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዓለም አቀፍ ስደተኞች ተቀብላ በማስተናገድ የምታደርጋቸውን ሰብዓዊ ተግባራትን አድንቀው ለዚህ ሀገራቸው ተገቢውን ሁሉ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል፡፡