ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ወደ ሰላማዊ መድረክ እንዲመጡ ጥሪ አቀረቡ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ወደ ሰላማዊ መድረክ እንዲመጡ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9 ቀን 2017ዓ.ም. ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ጽንፈኝነት እና ግጭት ማንንም እንደማይጠቅም በመገንዘብ ወደሰላማዊ መድረክ እንዲመጡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ መንግሥት ሁልጊዜም ቢሆን ለሰላም በሩ ክፍት በመሆኑን አረጋግጠዋል።
ዛሬ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች፣ የገጠር ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ህዝቡ ”ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ በነቂስ ወጥቶ ላሳየው የሰላም የድጋፍ ሰልፍ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡
ሰላም ወዳዱ ህዝብ መንግሥት ለሰላም እያቀረበ ያለውን ተደጋጋሚ ጥሪ በመደገፍና ፅንፈኝነትን በማውገዝ የታጠቁ ቡድኖች ወደ ሰላም እንዲመጡ ጥሪ አቅርቧልም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም የአማራ ክልልን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁሉም ለሰላም ዘብ ሊቆም ይገባል ብለዋል፡፡
መንግሥት ሁልጊዜም ቢሆን ለሰላም በሩ ክፍት በመሆኑ ትጥቅ ያነሱ ቡድኖች ጽንፈኝነት እና ግጭት ማንንም እንደማይጠቅም በመገንዘብ ወደሰላማዊ መድረኩ እንዲመጡ ጥሪ እናቀርባለን ነው ያሉት፡፡