መንግስት አሁንም ያለው አቋም ግጭቶችና አለመግባባቶች በሰላም እንዲፈቱ ነው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ሰላም ሚኒስቴር በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰላምና ደህንነትን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት መንግስት አሁንም ያለው አቋም ግጭቶች እና አለመግባባቶች በሰላም እንዲፈቱ ነው ያሉ ሲሆን ሰላም ለሌሎች የልማት ሥራዎች አስፈላጊ መሆኑን አንስተው ፤ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጋር ንግግር እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን፤ ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን፤ አንፈልገውም ሲሉም በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሰላም አማራጭ ውጤቱ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ፥ መንግስት ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ ቅድሚያ ሰጥቶ መስራቱን ይቀጥላልም ብለዋል፡፡

አሁንም ያለን አቋም የትኛውም ዓይነት አለመግባባት በሰላም እንዲፈታ ነው ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ ሆኖም ግን የትኛውም አካል በኃይል እና ጥላቻ መጠፋፋትን እንጂ ዓላማውን ማሳካት አይችልም ብለዋል፡፡