የህብር ቀን አከባበርን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የ"ሕብር ቀን" በሚመለከት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

መግለጫውን የሰጡት በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ቀኑ የ"ሕብር ቀን" የተባለበትን ምክንያት ሲያብራሩ ‹‹ኢትዮጵያ ሀገራችን የጥንታዊ ታሪክ ባለቤት፤ በዚህ ጥንታዊ የረጅም ጊዜ ታሪኳ ብዙ ውጣ ውረዶችን ያለፈች በውስጧም በህብር የሚገለፁ የሃይማኖት፣ የብሔር፣ የቋንቋ፣ የባህል፣ የመልክዓ ምድር አቀማመጥ እና የአየር ጸባይ ህብር መገለጫ ሀገር ናት›› ብለዋል፡፡

‹‹ይህም ሕብር ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን ባላፉት ዘመናት ቅድመ አያቶቻችን በነበሩት የጂኦ-ፖለቲካ እና በውስጧ ካለው እምቅ ሀብት አኳያ የቋመጡት የተለያዩ አካላት ሙከራ ቢያደርጉም ይህንን ሕብር ተጠቅመው በደም መስዋዕት የጠበቋት ሀገር ነች፡፡ አድዋን የመሰሉ በዓለም የሚታወቁ የአኩሪ ታሪክ ባለቤትነት ያጎነጸፈንን ሕብር ሁሌ መዘከር ብቻ ሳይሆን፤ ይንን ሕብር ለዘላቂ፣ ጠንካራ፣ አካታች፣ ሀገራዊ ግንባታ እና ለዘላቂ አዎንታዊ ሰላም ግንባታ መጠቀም ያስፈልጋል›› ብለው ቀጣይም መሰል ነገሮች ሲመጡ ሕብርን መጠበቅ የኢትዮጵያዊነትን ማንነት መጠበቅ መሆኑን በአጽንዖት ገልፀዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘው ‹‹ሕብራችንን መጠበቅ የኢትዮጵያን ታሪክ መጠበቅ፣ ሕብርን መጠበቅ የቅድመ አያቶቻችንን አደራ መጠበቅ እና የሉዓላዊነታችን መሠረት መሆኑን መግለጽ ስለሚያስፈልግ ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ የሰላም ሚኒስቴር፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በጋራ የተለያዩ አጋር አካላትን በማስተባበር የሕብራችን መገለጫ የሆኑ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች እና የኃይማኖት አባቶችን ጭምር ባሳተፈ መልኩ ሕብርነታችን፣ አብሮነታችን በፈታኝ ጊዜ በአብሮነት ያሳለፉትን ጊዜ እየዘከሩ፤ ትናንትን እያስታወሱ፣ ኢትዮጵያዊ ሕብርነታቸውን እና በሕብርነት ውስጥ ያለውን አንድነት እያጠናከሩ ለቀጣይ አብሮነት ቃል ኪዳን የሚገቡበትና ስጦታዎችን የሚሰጣጡበት ልዩ መርሐ ግብር ነው›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

መርሐ-ግብሩም ‹‹ሕብራችን ለሰላማችን›› በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን በሰላም ሚኒስቴር፣ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በጋራ የተዘጋጀ ነው፡፡