የሰላም ሚኒስቴርና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. የሰላም ሚኒስቴርና የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የጋራ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝም እና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር አቶ ቸሩ ጌታ ገነነ የሰላም ሚኒስቴርና የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ህብረ ብሄራዊ አንድነት እንዲጎለብት ፣የህዝቦች አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር ፣የፌዴራል ስርዓቱ እንዲጠነክር፣ ፣በክልሎች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በመከላከልና በመፍታት እንዲሁም ህገመንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ጉዳዮችን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ የጋራ ተልዕኮ ያላቸው ተቋማት ናቸው ብለዋል።

እነዚህን ተልዕኮዎች ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማሳካት ሁለቱ ተቋማት በትብብርና በአጋርነት መስራት እንደሚገባ መግባባት ላይ መድረስ በመቻሉ ዕቅዱ መዘጋጀቱን ክቡር ሚኒስትር ዴዔታው ተናግረዋል።

የጋራ ዕቅዱ ዓላማ አቅምን በማቀናጀት ዘላቂ ሰላምን መገንባት፣የህዝቦች ትስስርና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር ፣ግጭቶችን መከላከልና መፍታት፣በፌዴራል ስርዓቱና በመንግስታት ግንኙነት ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ በማስፋት የተዋረድና የጎንዮሽ ግንኙነት መድረኮች ተቋማዊ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል።

በቀረበው ዕቅድ ላይ ከሁለቱ ተቋማት የተገኙ አመራሮች እና ባለሙያዎች አስተያየት ሰጥተውበት ወይይት ተደርጎበታል።