አዎንታዊ እና ዘላቂ ሰላም
አዎንታዊ እና ዘላቂ ሰላም
ለዘላቂ ሰላም አስተማማኝ መሠረት ተጥሏል ለማለት ግጭት እና አለመግባባት የሚፈጠርበት ምንም ዓይነት አጋጣሚ የለም ማለት አይደለም። ፈጽሞ ግጭቶች አይነሱም ማለትም አይደለም። አዎንታዊ ዘላቂ ሰላም አለመግባባቶች ቢፈጠሩ መፍትሔ የሚያገኙበት አሠራር መኖሩ ለአዎንታዊ ሰላም መፈጠር መሠረት ነው።
አዎንታዊ ሰላም ችግሮች ሲፈጠሩ መፍትሔ እየፈለገላቸው ራሱን ጠብቆ የሚያቆይ ሰላም ነው። የአዎንታዊ ሰላም መኖር ለዘላቂ ሰላም ዋስትና ነው።
በአንፃሩ አዎንታዊ ሰላም ሳይኖር አሉታዊ ሰላም ሊኖር ይችላል። ማኅበራዊ ችግሮች ሳይፈቱ ግልጽ ሁከቶችን ብቻ በማስወገድ ወይም በማፈን አሉታዊ ሰላምን ማስፈን ይቻላል። ነገር ግን አዎንታዊ ሰላም ከዚህ በተለየ መልኩ ማኅበረሰባዊ መሠረት ያለው፣ ለሁሉም የሚያስፈልግ፣ የሁሉም ነገር መሠረት መሆኑን ሁሉም የሚረዳው እና እያንዳንዱ ሰው ባለቤት ሆኖ የሚጠብቀውና የምንከባከበው ሰላም ነው አዎንታዊ ሰላም የሚባለው፡፡
አዎንታዊ ሰላም እንዲሰፍን ለሰላም እንቅፋት የሚሆኑ አፍራሽ አስተሳሰቦችን እና ድርጊቶችን በተለይም ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ነጠላ ትርክቶችን በጋራ ጥረት መመከት፣ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን መደገፍ፣ ሰላምን በመሻት እና ከመሻት ባሻገር ለሰላም ተግቶ መሥራት አስፈላጊ ነው።
ሰላም ለኢትዮጵያ !