የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ከሩዋንዳ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቪንሰንት ቢሩታ ጋር ተወያዩ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ከዶ/ር ቪንሰንት ቢሩታ ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት አደረጉ።

ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም "የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው አህጉር አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ከተገኙት የሩዋንዳ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቪንሰንት ቢሩታ ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ የሁለቱን ሀገራት ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ የጋራ ልምድንና እውቀትን በመጠቀም ለሰላም ግንባታ ስራዎች ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችል ነው ተብሏል።