Asset Publisher

ትንታኔ

የሀገረ ብሔር ግንባታ/ Nation Building ምንነት

ሀገረ ብሔር ግንባታ/Nation Building/ ስንል በአንድ ሀገር የሚኖሩ ህዝቦች የጋራ ማንነታቸውን፣ የጋራ አመለካከታቸውን ፣ እምነታቸውንና የጋራ እሴታቸውን የሚገነቡበትና የሚያዳብሩበት ሂደት ነው፡፡ ይህም በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ካለፈው ታሪካቸው እና ከአሁኑ የጋራ አኗኗራቸው የመነጨ የጋራ አመለካከት እሴቶችና እምነቶች የሚገነቡበት እና ከሌሎች ጎረቤት ሀገራትና ህዝቦች የሚለያቸው የጋራ መለያ ባለቤት የሚሆኑበት ሂደት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

ባህላዊ ግጭት አፈታት ስርአቶች ለሰላም ያላቸው ፋይዳ

በሀገራችን የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች ያሏቸውን የግጭት አፈታት ስርአቶች ብንመለከት ግጭት ውስጥ በገቡ ወገኖች መካከል እርቅ እንዲወርድ በማድረግ የተወሰነ ሳይሆን፤ ለግጭት ዘላቂ መፍትሄ በመፈለግ በማህበረሰቡ ዘንድ በግጭቶች ምክንያት ደፍርሶ የነበረውን ሰላም መልስ እስኪያገኝ ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን በዚህም በግጭት ምክንያት የተቋረጡ ማህበራዊ ግንኙነቶቻቸውን በመጠገን በማህበረሰቡ ዘንድ ዘላቂ የሆነ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖር ያደርጋል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ

ፌዴራሊዝም እና የፌዴራል ሥርዓት 

የፌደራሊዝም እና መንግስታት ግንኙነት  መነሻ የፌደራል ስርአቱን አሰመልክቶ ከፌዴራል መንግስት የሚተላለፍ ትዕዛዝና ጥያቄ፣ ከክልሎች የሚቀርብ ጥያቄ እንዲሁም ከተለያዩ የመንግስታት ግንኙነት ፎረሞችና የምርምር ውጤቶች የተገኙ መረጃዎችና የተለዩ ችግሮችና ክፍተቶች ሊሆን ይችላል፡፡ መድረሻውም እነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተውና ክፍተቶቹና ችግሮቹም ተቀርፈው የተመሰረተ ጠንካራና ቀጣይነት ያለው የፌደራል ስርአት እና መንግስታት ግንኙነት ተግባራዊ ማድረግ ይሆናል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ

ማህበራዊ ሃብቶች አለመግባባቶችን ለመፍታት ያላቸው ሚና

ማህበራዊ ሃብቶች አብሮ በመኖር ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችንና ግጭቶችን ከመፍታት አንፃር ያላቸው ሚና አይተኬ ነው:: የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባር መካከል በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር እና በህብረተሰቡ መካከል የሰላም፣ የመከባበርና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር የግንዛቤና ንቅናቄ ስልቶችን ቀይሶ መስራት ነው

ተጨማሪ ያንብቡ

ማህበራዊ ሀብቶች ለዘላቂ ሰላማችን

በመላው የሀገራችን ክፍል የሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ዕርቅና ሰላምን ለማምጣት ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች አንዱ የሽምግልና ስርዓት ነው፡፡ይህ ስርዓት በተለያዩ ስያሜዎች በሁሉም ማህበረሰብ ዘንድ ግጭቶችንና አለመግባባቶችን ለመፍታት እስካሁን ድረስ በስፋት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ