የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ የጋራ ምክክር ተደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ነሐሴ 27 ቀን 2016 . የሰላም ሚኒስቴር ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር የሚያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የሰላምና ፀጥታ ተቋማት የጋራ መድረክ 7ኛው ጉባዔ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም:- የኢትዮጵያ መንግሥት የተዛቡ ትርክቶችን በጥንቃቄ ፈትሾ በምትኩ ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያግባባ፣ የቀደሙ ትርክቶችን ጉድለት የሚሞላ፣ መንግሥታት በተቀያየሩ ቁጥር የሚቀየር ሳይሆን በዘላቂነት ሀገር ለመገንባት የሚያስችል፣ ብዝኃነትን መሠረት ያደረገ ሀገራዊ አንድነትን እና ኢትዮጵያዊነትን መዳረሻው ያደረገ ገዢ ትርክት ለመቅረጽ ጥረት ማድረጉን በጉባዔው መክፈቻ ላይ ባሰሙት ንግግር ገልጸዋል፡፡ ገዢ ትርክት ወደ ምልዐተ ሕዝቡ ወርዶ ውይይት እንዲደረግበትና መግባባት እንዲፈጠርበት ለማድረግ ሰፊ ሥራ መሠራቱንም አሳውቀዋል፡፡

የሀገር ግንባታ ከሰላም ግንባታ ሥራ ተነጥሎ የማይታይ መሆኑን የገለጹት ክቡር አቶ ብናልፍ 2016 . በሰላም ግንባታ ዙሪያ በርካታ ተግባራት የተከናወኑ መሆኑን፤ በተለይም አዎንታዊ ሰላም የመገንባት ሥራ የላቀ ትኩረት ተሰጥቶት የተከናወነ ተግባር መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ግጭትን ለመፍታት በተደረጉ ጥረቶች የተገኙ ውጤቶች አብዛኛው የሀገራችን አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እንዲኖራቸው የስቻለ ቢሆንም አሁንም ግጭት ያለባቸው የሀገራችን አካባቢዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ 2015 እና 2016 . የተገኙ ልምዶችን በመጠቀም የሚታዩ ግጭቶች እንዲፈቱ፤ የትኛውም ዓይነት ጥያቄ አለኝ የሚሉ አካላት አክሳሪ ከሆነ ግጭት ወጥተው ወደ ሰላማዊ ወይይትና ድርድር መጥተው ችግሮች እንዲፈቱ እና ጠንካራ ሀገርና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እንደሚሠራም ገልጸዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ እንደሻው ጣሰው ክልሉ ከተመሠረተበት አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለሰላምና ፀጥታ ችግሮች መንስዔ እየሆኑ ለነበሩ ያደሩና የቆዩ፤ የአደረጃጀት፣ የመዋቅር፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ በመስጠት የሰላም ችግሮችን መቀነስ የተቻለ መሆኑን አሳውቀው በክልሉ የሰላም ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶት የሚሠራ ሥራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ አመራሮች፣ የፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የሚሊሻ ኃላፊዎች እና የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በሀገሪቱ የተረጋጋ ሰላም ለማስፈን መዋቅራዊ አደረጃጀቶችን በማጠናከር የየአከባቢዎችን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ጠንካራ እና የዘመነ የትብብር አሠራር መከተል እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

በመጨረሻም ሁሉም የሰላምና ፀጥታ ተቋማት የሚታዩ የሰላም ችግሮች ተፈተው የሰላም ግንባታ ሥራው የላቀ ውጤት እንዲያመጣ በቀጣይ በትኩረት ተቀናጅቶ መሥራት በሚያስፈልጉ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።