ፌዴራሊዝም እና የፌዴራል ሥርዓት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ስልጣን እና ተግባር መካከከል በመንግስታት መካከል ያሉትን ግንኙነቶች በመከታተል ክፍተቶችና ችግሮች ለይቶ በፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ በአሰራር ማዕቀፎችና ፕሮሲጀሮች በማጠናከር እንዲሁም ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመስማማቶችን (ግጭቶችን) በድርድር፣በመተባበበር እና በአጋርነት እንዲፈቱ በማስወገድ ወይም በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን በመፍጠር የዳበረና ቀጣይነት ያለው የፌደራል ስርአትና የተጠናከረ የመንግስታት ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ በፌዴራል ስርዓቱ ውስጥ የጋራ የሆነ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ያስችላል፡፡

የፌደራሊዘም እና መንግስታት ግንኙነት መነሻ የፌደራል ስርአቱን አሰመልክቶ ከፌዴራል መንግስት የሚተላለፍ ትዕዛዝና ጥያቄ፣ ከክልሎች የሚቀርብ ጥያቄ እንዲሁም ከተለያዩ የመንግስታት ግንኙነት ፎረሞችና የምርምር ውጤቶች የተገኙ መረጃዎችና የተለዩ ችግሮችና ክፍተቶች ሊሆን ይችላል፡፡ መድረሻውም እነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተውና ክፍተቶቹና ችግሮቹም ተቀርፈው የተመሰረተ ጠንካራና ቀጣይነት ያለው የፌደራል ስርአት እና መንግስታት ግንኙነት ተግባራዊ ማድረግ ይሆናል፡፡

ፌዴራሊዝም የፌዴራል ሥርዓት ታካዊ ዳራ

በዓለማችን ዘመናዊነት እየተስፋፋ፣ የመረጃ ልውውጥ እያደገና የዴሞክራሲ ባህል እየጎለበተ ሲሄድና ሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ የሚያደርጉት ዝውውር እየጨመረ በመምጣቱ ብዝሃነት የበርካታ ሃገራት መገለጫ እየሆነ መጣ፡፡ ስለሆነም ብዝሃነትን ማስተናገድ የሚችል ስርዓት የመገንባት ጉዳይ ችላ የማይባል ጉዳይ ሆነ፡፡ በተለይ የማንነትና የእኩልነት ጉዳይ የፖለቲካ ጥያቄ በሆነበት ሀገር ጥያቄውን በፍትሃዊነት ማስተናገድ ትልቅ ፈተና እየሆነ መጥቷል፡፡ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ማንነትና በቋንቋ የመጠቀም መብት፣ የራስ አስተዳዳርን የማም ፍላጎት፣ ፍትሃዊ የሥልጣን ክፍፍልና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከሀገር ሀገር እየተስፋፉ በመሄዳቸው መፍትሄ የሚያሻቸው ጉዳዮች ሆነዋል፡፡