Continguts més visitats

null ዓለም ዓቀፍ የሃይማኖት ኮንፈረንስ የፓናል ውይይይ ተካሄደ

እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም ዓቀፍ የሃይማኖት ኮንፈረንስ ላይ  ''ሃይማኖታዊ አስተምሮዎች ለሰላም መስፈን ያላቸው ሚና እና  በኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች  ተከባብረውና  ተዋደው ከመኖር አንፃር ያለው ልምድ ''አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሂዷል ።

 

በፓናል ውይይወቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፣ ዕስልምና እና ወንጌላዊያን ሃይማኖቶች ስለ ሰላም ያላቸው አስተምሮዎች እና እርስ በዕርስ ተከባብረው ከመኖር አንፃር ያላቸው ልምድ ቀርቦ ውይይት ተካሂደል፡፡

የፖናል ውይይቱን የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) መርተውታል።