ማህበራዊ ሃብቶች አለመግባባቶችን ለመፍታት ያላቸው ሚና
ማህበራዊ ሃብቶች አለመግባባቶችን ለመፍታት ያላቸው ሚና
ማህበራዊ ሃብቶች አብሮ በመኖር ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችንና ግጭቶችን ከመፍታት አንፃር ያላቸው ሚና አይተኬ ነው:: የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባር መካከል በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር እና በህብረተሰቡ መካከል የሰላም፣ የመከባበርና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር የግንዛቤና ንቅናቄ ስልቶችን ቀይሶ መስራት ነው።
ይህ ሀገራዊ ተልዕኮ ይሳካ ዘንድ እንደ ሀገር በማህበረሰቡ ውስጥ ለዘመናት የዳበሩና የተከማቹ ማህበራዊ ሃብቶች እና ዕሴቶችን ለሰላም ግንባታ እና ለሀገር ግንባታ ማዋል ደግሞ ወቅቱ የሚጠይቀው የቤት ሥራ ነው፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ያሉንን ማህበራዊ ሃብቶች ለሰላም እና ለሀገር ግንባታ ለማዋል ትልልቅ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
እንደ ሀገር በማህበረሰቡ ውስጥ ለዘመናት የዳበሩና የተከማቹ ማህበራዊ ሃብቶች እና ማህበራዊ ዕሴቶች ያሉን ሲሆን የሰላም ሚኒስቴር በህግ ከተሰጡት ተልዕኮዎች አንፃር እነዚህ ማህበራዊ ሃብቶች ሰላምን ለመገንባትና ሀገርን ለመገንባት ያላቸውን ሚና በመረዳት ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ ነው፡፡
ማህበራዊ ሃብቶች ካላቸው ሀገራ ፋይዳዎች መካከል የመጀመሪያው ማህበረሰብን ማስተሳሰር ፣ ማዋህድ፣ ማግባባት እና አብሮ በመኖር ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባበቶችንና ግጭቶችን መፍታት ሲሆን ማህበራዊ ሃብቶች ከሌሎች የግጭት መፍቻ ዘዴዎች አንፃር ሲታይ ወጪ ቆጣቢ እና ዕውነተኛ እርቅ ለማውረድ ሚናቸው አይተኬ ነው፡፡
እንደ ተቋም ሰላም ግንባታን ስናስብ አንዱ የሰላም መገንቢያ ምሰሶ በማህበረሰቡ ውስጥ ለዘመናት የቆዩ የግጭት መፍቻ ስልቶችና የማህበራዊ ግንኙነቶች ናቸው፤ እነዚህን ማህበራዊ ሃብቶች ለመጠበቅ እና በተገቢው መንገድ ለማዋል በጥናት ላይ የተመሰረቱ ስራዎች እየተሰሩም ይገኛል፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያ!