ዓለም አቀፍ የኃይማኖት ኮንፈረንስ የፎቶ ኤግዚቪሽን
التطبيقات المتداخلة
ناشر الأصول
የሰላም ሚኒስቴር ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ከሚገኘው ከመሐመድ ቢን ዛይድ ፎር ሁማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ኮንፈረንስ ላይ ሀገራችን ያላትን የረጅም ዘመናት የሃይማኖት መከባበርና አብሮነት ለዓለም ለማሣየትና ለማስገንዘብ ያለመ የፎቶ ኢግዚቢሽን ተዘጋጅቷል ።
የፎቶው ኢግዚቢሽኑ በኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ክቡር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ፣ በሰላም ሚኒስቴር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም እና በሐይማኖት አባቶች ተመርቆ ተከፍቷል።
የሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ የኢትዮጵያ የሃይማኖቶች አባቶች ፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ፣የክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች፣በሐይማኖት እና ሰላም ላይ ትኩረት አድርገው ጥናትና ምርምር ያካሄዱ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምስራቅ አፍሪካ፣ የሩሲያ፣ የሞሮኮ እና የደቡብ አፍሪካ የሃይማኖት ተቋማት እና አለም አቀፍ ድርጅቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በኮንፈረንሱ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ناشر الأصول
የክቡር የሚኒስትሩ መልዕክት
አቶ መሐመድ እድሪስ መሐመድ የኢፊዲሪ የሰላም ሚኒስትር
የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ዋና ዋና ተግባራት መካከል ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም ማስፈን፣ ብሔራዊ መግባባትና አገራዊ አንድነትን ማጎልበት፣ የፌዴራል ሥርዓቱ የግንኙነት ማዕከል ሆኖ ማገልገል፣ ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከልና ማስተዳደር ሲሆን እነዚህን ተግባርና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ያከናውናል።
ተጨማሪالتطبيقات المتداخلة
ناشر الأصول
ناشر الأصول
ትንታኔ
ህብረ-ብሔራዊ የፌዴራል ስርዓት ለዘላቂ ሰላም
በሀገራችን ብዙህነትን እውን ለማድረግ ከሚሰሩ ስራዎች ውስጥ በህብረ ብሄራዊ የፈዴራል ስርዓቱ ላይ በቂ ግንዛቤ፤ መግባባት እና የአመለካከት የበላይነት በሁሉም ደረጃ ማረጋገጥ ይገኝበታል፡፡ በህብረ-ብሄራዊ የፌዴራል ስርዓታችን ውስጥ በተፈጥሮ ያለው ልዩነት በሥራና በሂደት ወደ ብዙህነት ሲያድግ፤ ህብረ ብሄራዊነታችን በተግባር፤ በሥራ ሲረጋገጥ ሀገራዊ ውበታችንና ኩራታችን ይሆናል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ“በጎነት ለአብሮነት”
የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ዓላማ ኢትዮጵያ ያሏትን መልካም እሴቶች፣መርሆዎች፣ የሀገርና የሕዝብ ፍቅር ለወጣቱ ትውልድ በማስተላለፍ የወጣቶችን ምክንያታዊነትን፣ የሕይወት መምራት ክሕሎትን፣ የሥራ ባሕልን፣ መልካም ሥነ ምግባርን በማጎልበት አገራዊ አንድነትን እና ብሔራዊ መግባባትን በማስረጽ ዘላቂ ሰላም መገንባት የሚያስችል ነው ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ