አንድነትና አብሮነት ለብሔራዊ ክብር!

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የተለያዩ ምክንያቶችን እና ጊዜያትን ጠብቀው እየተነሱ ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለሀገራዊ መረጋጋት አደጋ ሲሆኑ የነበሩ ችግሮች በሀገር ወዳድ ጀግኖቻችን ተቀልብሰው የተከበረች እና የነፃነት ተምሳሌት የሆነች ሀገር እንድንረከብ አስችሎናል፡፡

ቀደምት ጀግኖቻችን ችግሮችን ተፋልመው በድል ሲሻገሩ የነበሩት በመለያየት ሳይሆን በጋራ ቆመው ፈተናዎችን መመከት ስለቻሉ ነው፡፡ ችግሮችን ሲሻገሩ የነበሩት ጥብቅ የሆነ አንድነትና አብሮነት፤ ጥልቅ የሆነ የሀገር ፍቅር ስለነበራቸው ነው፡፡

እነሱ ፈተናዎች አልፈው ክብሯን እና ነጻነቷን አስጠብቀው ያወረሱን ሀገር ሰላም እንድትሆን ይህ ትውልዱ ከፋፋይ የሆኑ አመለካከቶችን በመተው ፤ በአብሮነት በመቆም ፤ በውስጥም በውጭም እየተቃጣ ያለውን የሰላም እጦት ችግር መመከት ይኖርበታል፡፡ ሰላማችንን እውን ማድረግ የምንችለውም ሆነ ሀገራችን ታፍራና ተከብራ እንድትኖር የምናደርገው እኛው ነን፡፡

አባቶቻችን መስዋዕት ከፍለው ሉዓላዊነቷ የተከበረ ሀገር እንዳስረከቡን ለአፍታም መዘንጋት አይገባም። እነሱ ብዙ ዋጋ ከፍለው ከነክብሯ ያስረከቡንን ሀገር እኛም ጠብቀን፣ አስከብረን፣ አልምተን ለቀጣይ ትውልድ ማስረከብ የኢትዮጵያዊነት ታሪካችን ነው፡፡

ሰላም ለኢትዮጵያ !