ዓለም አቀፍ የኃይማኖት ኮንፈረንስ የፎቶ ኤግዚቪሽን "ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም"

内嵌的应用

资产发布器

null ዓለም አቀፍ የኃይማኖት ኮንፈረንስ የፎቶ ኤግዚቪሽን

የሰላም ሚኒስቴር ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ከሚገኘው ከመሐመድ ቢን ዛይድ ፎር ሁማኒቲ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር   እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ኮንፈረንስ ላይ ሀገራችን ያላትን የረጅም ዘመናት የሃይማኖት መከባበርና  አብሮነት ለዓለም ለማሣየትና ለማስገንዘብ  ያለመ የፎቶ ኢግዚቢሽን ተዘጋጅቷል ።

የፎቶው ኢግዚቢሽኑ  በኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ክቡር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ፣ በሰላም ሚኒስቴር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም እና በሐይማኖት አባቶች ተመርቆ ተከፍቷል።

የሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ  የኢትዮጵያ የሃይማኖቶች አባቶች ፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ  ፣የክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች፣በሐይማኖት እና ሰላም ላይ ትኩረት አድርገው ጥናትና ምርምር ያካሄዱ  የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምስራቅ አፍሪካ፣ የሩሲያ፣ የሞሮኮ እና የደቡብ አፍሪካ የሃይማኖት ተቋማት እና አለም አቀፍ ድርጅቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው  እንግዶች በኮንፈረንሱ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

资产发布器

የክቡር የሚኒስትሩ መልዕክት

አቶ መሐመድ እድሪስ መሐመድ የኢፊዲሪ የሰላም ሚኒስትር

የሰላም ሚኒስቴር በአዋጅ ከተሰጡት ዋና ዋና ተግባራት መካከል ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም ማስፈን፣ ብሔራዊ መግባባትና አገራዊ አንድነትን ማጎልበት፣ የፌዴራል ሥርዓቱ የግንኙነት ማዕከል ሆኖ ማገልገል፣ ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከልና ማስተዳደር ሲሆን እነዚህን ተግባርና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ያከናውናል።

ተጨማሪ

内嵌的应用

资产发布器

ትንታኔ

አሰባሳቢ ትርክት ለብሔራዊ መግባባት

አፍራሽ ትርክቶች በግልም ሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ጎታች አስተሳሰቦችን ከማስረፅ በተጨማሪ ለምናስባቸው ግለሰባዊ፣ ማኅበረሰባዊና ሀገራዊ ግቦች ስኬትን ሳይሆን ውድቀትን ያመጣሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ

የሰላም እሳቤ እና አስፈላጊነት

መዋቅራዊ የሰላም ግንባታ ጅምሮችን የሚያጎለብት፣ ማኅበረሰባዊ እሴቶችን ያማከለ፣ እና ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚያካትት ሰላምን ይበልጥ የሚያፀና ሥራ መሥራት ከሀገራችን ተሻግሮ ለቀጣናው ሁለንተናዊ ለውጦች ፋይዳው የላቀ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ

资产发布器

ቪዲዮ ዜና

ኢትዮጵያዊ ማነው? ኢትዮጵያዊነትስ ምንድነው? | የታሪክ ወግ ከኸይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) | የወል እውነት | ጋር
የጎንደር ቃልኪዳን ቤተሰብ ሀገር አቀፍ የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ያስተላለፉት መልዕክት
አንጻራዊ ሰላምን ማፅናት
ባህላዊ የግጭት አፈታት እሴቶችን በመጠቀም የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት ተቋማት መሪዎች ሰላምን ለማስፈን የሚያበረክቱትን አስተዋፆ |selam |peace