ወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ ተጀመረ
ወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ ተጀመረ
ሰኔ 20 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ለተመደቡ የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከአዲስ አበባ የሰላም ሠራዊት ጋር በማስተሳሰር ለአንድ ወር የሚቆይ የክረምት በጎ ፈቃደ አገልግሎት ተጀምሯል፡፡
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ወጣቶችን ትኩረት አድርጎ የሚሰራ በመሆኑ ከመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ያሰባሰበ ወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ቀርፆ ወደ ትግበራ መግባቱን በመግለጽ፤ ይህም ተግባር ለሀገር ግንባታ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት ለአንድ ወር የሚቆየው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ትኩረት አድርጎ የሚሰራው በማህበራዊ ትስስር፣ በልማት ሰራዎች እና በማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ ነው ብለዋል፡፡
ከአዲስ አበባ የሠላም ሰራዊት ጋር በማስተሳሰር ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ ባሉ አደረጃጀቶች አብሮ ይሰራል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ተማሪዎች በበኩላቸው፤ ይህ ተግባር አብሮነትን በማመጠናከር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በማጉላት ጠንካራ ሀገረ-መንግስት ለመገንባት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡