የ2016 ዓ.ም የሀገር አቀፍ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 12/2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር  ጋር በመተባበር የ2016 ዓ.ም የሀገር አቀፍ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የንቅናቄ መድረክ "በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል :: 

በመድረኩ ላይ የክብር እንግዳ የሆኑት የኢፌዲሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በተጀመረው የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ 34 ሚሊየን በላይ በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ የበጎፈቃድ አገልግሎት ስራ የአንድ ክረምት ስራ ብቻ ሳይሆን የእለት ተዕለት ስራችን መሆን ይኖርበታል ብለዋል በመሆኑም ይህ ስራ ቀጣይነት እንዲኖረው እና ይህንን ግብ ለማሳካት ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባናል ብለዋል። 

በመድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም ይህ የንቅናቄ የበጎፈቃድ የአገልግሎት ስራ ብዝሀነትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ ሀገር ለመገንባት፣ የተረጋጋና ዘላቂ ሰላም ለማስፈንና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።

ክቡር አቶ ብናልፍ አብሮነትን ለመፍጠር ዋናው መሳሪያ በጎነት መሆኑን የገለጹ ሲሆን በጎነት ሰውን ማዕከል ያደረገ በመሆኑ ለራስ ሳይሆን ለሌሎች መኖርን ባህል ያደረገ ማህበረሰብ መገንባት ይጠበቅብናልም ብለዋል። 

ስለሆነም በጎ ፈቃድ ወጣቶች ወደማያውቁት ክልል የሚሄዱ በመሆኑ የክልል ከፍተኛ አመራሮች የክልሉን ባህል፣ አኗኗር እና ቋንቋ እንዲያውቁ እድል እንድትፈጥሩላቸው እና ለስራው ስኬት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድትወጡ አደራ ብለዋል።