"የኢትዮጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ፤ ለልጆቼ ምንዳን አወርሳለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት ተካሄደ።

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ከተቋሙ ሴት  ሰራተኞች ጋር  "የኢትዩጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ፤ ለልጆቼ ምንዳን አወርሳለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት ተካሂዷል ፡፡ 

በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሰላም ሚኒስቴር የተቋማዊ ለውጥ ከፍተኛ ባለሞያ የሆኑት አቶ ከተማ ምርከና ሲሆኑ የዚህ መድረክ ዓላማ ሴቶች የራሳቸውን መብት በማስጠበቅ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለማሳደግ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ስለሆነም ሴቶች በሀገራዊ ሰላም ግንባታ ውስጥ ያላቸው ሚና ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸው፣ መብቶቻቸውን በማስከበርም ሆነ በሰላም ግንባታ ሂደቶች ውስጥ ድምጻቸውን እንዳያሰሙ የሚያደናቅፉ መዋቅራዊ፣ ተቋማዊ፣ልማዳዊ ተግዳሮቶች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡ 

ይህንንም መድረክ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ሴቶች  መብቶቻቸውን በማስከበር እና በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ያላቸው ሚና እንዲያድግ ባስተላለፉት የሰላም ጥሪ፤ ሴቶች የተለያዩ መድረኮችን በመቀጠም መብቶቻቸውን ማስከበር እንደሚገባቸው እና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባቸውም ተናግረዋል። 

በመድረኩ ላይ በሰላም ሚኒስቴር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ስራ አስፈጻሚ የሴቶችና ህጻናት አካቶ ትግበራ ባለሞያ የሆኑት ወ/ሮ ባንቺይርጋ አበበ  "የኢትዩጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ፤ ለልጆቼ ምንዳን አወርሳለሁ" የሚል ጹሁፍ ያቀረቡ ሲሆን "ራስን ማክበር"በሚል ርዕስ ደግሞ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ  ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ወጋየሁ ቢያድግልኝ ቀርቦ  ውይይት ተካሂዷል፡፡ 

በውይይቱ ማጠቃለያ የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና የዲሞክራሲ ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ ስመኝ ወልዴ ሰላምን ወደራሳችን በመጥራት እራሳችንን በማክበርና ለሌሎችም ክብርን መስጠት ይገባናል ብለዋል። እንዲሁም በተሰማራንበት የሥራ መስክ ውጤታማ በመሆን መስራት እንዳለብንም ተናግረዋል።