በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ የስድስት ወር አፈጻፀም እና የጋራ ትብብር ቻርተር ውይይት ተደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም (የሰላም ሚኒስቴር) የሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ያለፉትን የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም፣ የጋራ ትብብር ቻርተር እና በሰላም ግንባታ የስርዓተ ጾታ ማካተቻ ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

የሰላምና ጸጥታ ትብብሩ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን፣ ፈጣን ልማት ለማረጋገጥ፣ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ ለመገንባት፣ መልካም አስተዳደርን ለማሰፈን፣ የሕዝብን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ትስስራቸውን በማጎልበት የፌደራሊዝም ሥርዓቱን የማጠናከር ዓላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል፡፡ 

ውይይቱ የተደረገው ቻርተርና የጾታ ማካተቻ በሀገራችን እንዲመጣ የሚታሰበውን ዘላቂ እና አዎንታዊ ሰላም እውን ለማድረግ በጋራ ተቀናጅቶ ውጤታማ ሥራ ለመሥራት፣ ክልሎች ሁሉንም የማኅበረሰብ አካላት ያሳተፈ ቅንጅታዊ አሠራርን ማዳበር እንዲችሉ እና ልምድና ተሞክሮዎችን ከአንዱ ወደ ሌላው ወስዶ የሰላም ግንባታ ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ በትብብር መሥራት በሚቻልበት ግልጽ የሆነ የአሠራር ሥርዓት ለመፍጠር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡ 

የሰላም ሚኒስቴር በሕገ-መንግሥቱ በተሰጠው ስልጣን እና የሰላምና ጸጥታ ቢሮዎች በጋራ ፍላጎት የትብብር ቻርተሩን በስምምነት አጽድቀዋል፡፡ ቻርተሩ በክልሎች የሰላምና ጸጥታ ቢሮዎች መካከል ሲካሄድ በቆዩ እና በክልሎች ርስ በርስ ሲካሄድ በነበረው የጎንዮሽ ግንኙነት የተሠሩ ሥራዎችን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ለይቶ ለማስቀጠል እንዲሁም በየደረጃው ያሉ የሰላምና ጸጥታ ተቋማት የግንኙነት ሥርዓት የሚመራበት ቻርተር ማውጣትና መተግበር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የተዘጋጀ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የፌደራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ቸሩጌታ ገነነ በውይይት መድረኩ መዝጊያ “በሕዝቦች መግባባትና ስምምነት ላይ መሠረት ያደረገ አዎንታዊ ሰላም ለመገንባት፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ ነጻና ገለልተኛ የሆነ የፍትህ ሥርዓትን ለመገንባት አብሮነትን ማጠናከር፣ በአጋርነት መሥራት፣ ተከታታይነት ያላቸው ምክክሮችን ማድረግን ይጠይቃል” በማለት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ክልሎች ለሰላም ግንባታው በቅንጅት እንዲሠሩ ለማሳሰብም  “በአንድ አካባቢ ወይም በአንዱ ክልል የሚፈጠር ግጭት የሁሉም ክልሎችና የሀገሪቷ ችግር መሆኑን በመገንዘብ  በመተጋገዝ፣ በመተባበርና በናበብ መሥራት ያስፈልጋል” ሲሉ አክለዋል፡፡ 

መድረኩ ውጤታማ አፈጻፀሞችን አጠናክሮ፣ ልምዶችን አዳብሮ፣ በጋራ ሠርቶ ሀገራዊ ሰላምን ለማምጣት አጎራባች ክልሎች በአጋርነት ለመሥራት፤ ውጤታማነትን ከፍ የሚያደርጉ ስልቶችን ለመቀየስ የመከሩበት ነ