የሰላም ሚኒስቴር ሠራተኞችና አመራሮች ‹‹ከዕዳ ወደ ምንዳ›› በሚል መሪ ሐሳብ ውይይት አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥር 30/2016 . (የሰላም ሚኒስቴር)፣የሰላም ሚኒስቴር  ሠራተኞችና አመራሮች ‹‹ከዕዳ ወደ ምንዳ›› በሚል መሪ ሐሳብ ውይይት አድርገዋል፡፡

ሠራተኞችና አመራሮች ጥር 29-30/2016 . ባደረጉት የሁለት ቀን ውይይትሃብት የመፍጠር ጉዟችን ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች’’  እናአገልጋይ እና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ  ለጠንካራ መንግሥት ግንባታ’’  በሚል  ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

 

 የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት ቀልጣፋ የዘመነና የተገልጋዩን ፍላጎት የሚያሟላ እንዲሆን ለማድረግ ሲቪል ሰርቫንቱ የላቀ ሚና እንዳለው አስገንዝበው፤ ቀጣይ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስተካከልና ወደ ላቀ የአገልጋይነት ደረጃ ለማድረስ በመንግሥት ደረጃ የተሰጠውን ትኩረት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 

የተጀመረውን ሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ ከዳር ለማድረስ፤ ሀገሪቷ ያላትን እምቅ አቅም ጥቅም ላይ በማዋል ሃብት ለማፍራት እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት፤ በመንግሥት በኩል ተዘጋጅተው እንዲተገበሩ የወጡ ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞችና ዕቅዶች ውጤታማ ሊሆኑ በሚችሉበት አግባብ መምራት፣ መፈጸምና ማስፈጸም በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡