"አድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ ተካሄደ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ጥር 28/2016 . ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር እና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "አድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች የኃይማኖት አባቶች አባገዳዎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ተማሪዎችና ተጋባዥ እንግዶች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በዩኒቨርሲቲው  ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ በአድዋ ድልና በጠንካራ ሀገራዊ መንግስት ግንባታ ዙሪያ ሁለት የውይይት ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አካደሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንትና የፕሬዝዳንት ተወካይ የሆኑት ፕሮፌሰር መንግስቱ ኡርጌ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት የአድዋ ድል ለእኛ ኢትዮጵያዊያን ጦርነትን የማሸነፍ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በራስ የመተማመንና የመከባበር ባህልና እሴት ምንጭ ነው ብለዋል፡፡

ፕሮፌሰር መንግስቱ አክለውም የአድዋ ድል የተመዘገበው ኢትዮጵያዊያን ያለ ልዩነት ለሃገራቸውና ማንነታቸው ክብር ሲሉ በጋራ ዘምተውና ተዋድቀው የተመዘገበ ድል ነው፡፡ የሃገራችን ህዝቦች በአድዋና በሌሎች ጦርነቶች ወቅት የመተማመን ባህሪያቸውንና ባህላቸውን እጅግ አሳድገው ስለነበር ጦርነቱን እጅግ በላቀ ወኔና እኔ ቀድሜ ልሙት በሚል ተግባራዊ ድርጊት ጣፋጭ ድል ተቀናጅተዋል፡፡ ይህም ኢትዮጵያዊያን በዓለም ወንድሞችና እህቶች ፊት በልበ ሙሉነት እንዲቆሙ ያስቻለ ነው፡፡ በመሆኑም በሃገራችን ውስጥ በእኩል ተሳታፊነት ተጠቃሚነትና ነጻነት እንደ ህዝብ የምንኖርባትን ሉአላዊት ሃገር መገንባት እንዳለብን ያስተማረን ድል ነው ብለዋል፡፡

በኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር የሀገራዊ ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ተወካይ የሆኑት አቶ ብዙነህ ምክሩ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት የተለያዩ መንግስታት በተለያዩ ዘመናት ሀገሪቱን ሲያስተዳድሩ የየራሳቸውን ትርክት ፈጥረው ያንኑ ለማስረጽ ሞክረዋል፡፡

ይሁን እንጅ እነዚህ ትርክቶች የሃገራችንን ብዝሃነት ያላማከሉ የዜጎችን የጋራ ፍላጎትና መብት ማስከበር ላይ ያልተመሰረቱ በመሆናቸው ቅቡልነት ማግኘትና ህዝብን ለጋራ ዓላማ ማሰለፍ ባለመቻላቸው የተነሳ የግጭትና አለመግባባት መንስኤ ሆነው  በተለያዩ ጊዜያት የእርስ በእርስ ግጭቶችን ስናስተናግድ ኖረናል ብለዋል፡፡

የሀገራችን የሰላም እጦት ምንጮች ከሀገረ መንግስት ምስረታ ጋር በተያያዘ በተፈጠሩ ሀገራዊ የጋራ ግንዛቤዎችና ጠንክራ የሀገረ- መንግስትና የህብረ ብሔር ግንባታ ካለመጠናቀቅ ጋር የተያያዘ እንደሆነ አቶ ብዙነህ ተናግረዋል፡፡

 

አቶ ብዙነህ አክለውም በሀገረ-መንግስት ግንባታው ላይ ሁሉም ዜጋ እንደ ህዝብ በጋራ ለአንድ ዓላማ በመቆም የጋራ ለሆነችው ሀገራችን ጠንካራ ሀገረ-መንግስት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ላይ የበኩሉን አዎንታዊ አስተዋጽዖ ማበርከት ይገባዋል ብለዋል፡፡

ጽሁፍ ያቀረቡት / ተማም ሃጂ አደም እንዳሉት ከአድዋ ድል በዋናነት ልንማር የምንችለው አንድነትንና ወንድማማችነትን ነው፡፡ ያለጾታ ብሄርና ኃይማኖት ልዩነት በአንድነት ተሳትፈው ድል አድርገዋል፡፡ አሁንም በዚህ ዘመን የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀምና በአንድነት በመሰለፍ ለሃገር አንድነት እድገትና ብልጽግና ሰርተን የአባቶቻችንን ጀግንነት በልማት ልንደግመው ይገባል ብለዋል፡፡ ምንጭ:-የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ