ሰላም በሌለበት ትላልቅ ነገሮችን ማለም እንደማይቻል ተነገረ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

ክቡር አቢይ አህመድ (/) የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14 መደበኛ ስብሰባ ከምክር ቤት አባላት በፀጥታ ሰላም ጉዳይ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ‹‹ሰላም በሌለበት ትላልቅ ነገሮችን ማለም እንደማይቻል ጠቅሰው የፖለቲካ ፍላጎት ማሳኪያ መንገድ የኃይል አማራጭ መሆኑና ማንኛውም ችግር ሲያጋጥም ያንን ችግር በንግግር ለመፍታት ያለን ልምድ የቀነሰ ነው›› ብለዋል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ግጭት በተከሰተባቸው ክልሎች ከምሁራን የሚቀርቡ ከጦርነት በመለስ ሕዝብን የማያጋጭ፣ የሕዝቡን ጥያቄ የሚመልስ ለሰላምና አብሮነት የሚቀርቡ አማራጮች ካሉ የፌደራል መንግሥት ተባባሪ እንደሚሆን አሳውቀዋል፡፡ ተወያይተን እና ተስማምተን የሕዝቡን ይሁንታ ያገኘ ሐሳብ ዘላቂ ሰላም ያመጣል ብለን እናምናለን፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች የሕዝብ ጥያቄ የሰላም ጥሪ ይደረግ የሚል ስለሆነ የሰላም ጥሪ በተለያየ ጊዜ መደረጉን አስታውሰው አሁንም  በሰላማዊ መንገድ ገብቶ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ማድረግ የሚፈልግ ኃይል ካለ በራችን ክፍት ነው ብለዋል፡፡